የአዲስ አበባ ተስፋ ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ተደርገው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቻምፒዮንነቱን ያረጋገጠበትን ድል አስመዝግቧል፡፡
ትላንት ወጣቶች አካዳሚን የገጠመው ንግድ ባንክ 4-1 ያሸነፈ ሲሆን ተከታዩ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመከላከያ መሸነፉን ተከትሎ ንግድ ባንክ 2 ጨዋታ እየቀረው የ2008 የውድድረ ዘመን ቻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የ19ኛ ሳምንት ውጤቶች
ቅዳሜ ግንቦት 27 ቀን 2008
ኢትዮጵያ መድን 3-0 ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-1 መከላከያ
ሙገር ሲሚንቶ 1-0 ሰውነት ቢሻው
እሁድ ግንቦት 28 ቀን 2008
አዳማ ከተማ 1-0 ደደቢት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 4-1 ወጣቶች አካዳሚ
– ኢትዮጵያ ቡና በዚህ ሳምንት አራፊ ነው፡፡
– ሊጠናቀቅ 3 ሳምንት ብቻ ቀርቶታል፡፡