ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወላይታ ድቻ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-0 ወላይታ ድቻ


ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው ካለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ወላይታ ድቻም ለ9ኛ ተከታታይ ጨዋታ ላይ ግብ ሳይቆጠርበት ወጥቷል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

89′ ከፈቱዲን ከርቀት የተሻገረለትን ኳስ ስንታየሁ ተቆጣጥሮ ቢሞክርም ፌቮ አድኖበታል፡፡ ጥሩ ሙከራ ነበር

82′ አብዱልከሪም ሃሰን በቮሊ የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደ ላይ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
82′
ቢንያም በላይ ወጥቶ አምሃ በለጠ ገብቷል፡፡

81′ በጥሩ መልሶ ማጥቃት የመጣውን ኳስ ፈቱዲን ጀማል ቢያገነውምየመታው ኳስ ጥንካሬ የሌለው በመሆኑ ፌቮ አድኖበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
78′
በዛብህ መለዮ ወጥቶ ስንታየሁ መንግስቱ ገብቷል፡፡

75′ የሁለቱም እንቅስቃሴ በመሃል ሜዳ የተገደበ ነው፡፡ ኳስ ወደ ማጥቃት ወረዳ ሲደርስ ይቋረጣል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
72′
ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ወጥቶ ሲሳይ ቶሊ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
62′
እንዳለ መለዮ ወጥቶ ሰለሞን ሀብቴ ገብቷል፡፡

61′ ፊሊፕ ዳውዚ ከግብ ጠባቂው ፊት ለፊት ጣጣውን የጨረሰ ኳስ ቢያገኝም የመታውን ኳስ ወንድወሰን አሸናፊ ይዞበታል፡፡

55′ ንግድ ባንኮች በእንቅስቃሴ የተሻሉ ቢሆኑም የተጠቀጠቀውን የድቻ የተከላካይ መስመር ሰብረው ለመግባት ተቸግረዋል፡፡

47′ ኤፍሬም አሻሞ ከግራ መስመር ወደ ውስጥ በመግባት ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ለውጥ – ንግድ ባንክ
ስንታለም ተሻገር ወጥቶ አብዱልከሪም ሃሰን ገብቷል፡፡


እረፍት !!
የመጀመርያው አጋማሽ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
44′
ጉዳት ያጋጠመው ዮሴፍ ድንገቱ (4) ወጥቶ ኃይለየሱስ ብርሀኑ (16) ገብቷል፡፡

41′ የማዕዘን ምት ሲሻማ ዮሴፍ ድንገቱ ተጋጭቶ ወድቋል፡፡ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል፡፡

40′ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ወጥ እንቅስቃሴ እየታየ አይገኝም፡፡

30′ ፊሊፕ ዳውዚ ከግራ መስመር ወደ ግብ የላከውን ኳስ ወንድወሰን ደርሶ አውጥቶታል፡፡

22′ ታድዮስ ወልዴ አክርሮ የመታውን ኳስ ወንድወሰን አሸናፊ አውጥቶታል፡፡

18′ እንዳለ መለዮ ጥሩ የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ ቢያገኝም የመታውን ኳስ ፌቮ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

15′ ባንክ በኳስ ቁጥጥር የተሻለ ቢሆንም ወላይታ ድቻዎች በፍጥነት ወደ ግብ በመድረስ በኩል የተሻሉ ናቸው፡፡

9′ ፈቱዲን ከቀኝ መስመር ሰብሮ በመግባት የሞከረውን ኳስ ፌቮ ኢማኑኤል ይዞበታል፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በንግድ ባንክ አማካኝነት ተጀመረ፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ

1 ኢማኑኤል ፌቮ

15 አዲሱ ሰይፉ – 16 ቢንያም ሲራጅ – 5 ቶክ ጀምስ – 27 አንተነህ ገብረክርስቶስ

17 ስንታለም ተሻገር – 18 ታዲዮስ ወልዴ

21 ኤፍሬም አሻሞ – 80 ቢንያም በላይ – 2 ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን

9 ፊሊፕ ዳውዚ

ተጠባባቂዎች
64 ዳዊት አሰፋ
98 ዳንኤል አድሃኖም
12 አቤል አበበ
6 አምሃ በለጠ
11 አብዱልከሪም ሀሰን
19 ሲሳይ ቶሊ
10 ዳኛቸው በቀለ


የወላይታ ድቻ አሰላለፍ

12 ወንደሰን አሸናፊ

6 ተክሉ ታፈሰ – 27 ሙባረክ ሽኩር – 2 ፈቱዲን ጀማል

9 ያሬድ ዳዊት – 8 አማኑኤል ተሾመ – 4 ዮሴፍ ደንገቱ – 18 በድሉ መርዕድ – 17 በዛብህ መለዮ

10 እንዳለ መለዮ – 19 አላዛር ፋሲካ

ተጠባባቂዎች
1 መክብብ ደገፉ
3 ቶማስ ስምረቱ
14 ሰለሞን ሀብቴ
29 ፀጋ አለማየሁ
16 ሃይለየሱስ ብርሃኑ
20 ስንታየሁ መንግስቴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *