ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-1 አርባምንጭ ከተማ
77′ ደጉ ደበበ | 36′ ተሾመ ታደሰ
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተፈፅሟል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
90+5′ አመለ ሚልኪያስ ወጥቶ ታሪኩ ጎጀሌ ገብቷል፡፡
90+3′ ቅጣት ምቱን በሃይሉ ለተስፋዬ ሰጥቶት ተስፋዬ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
90+2′ ወርቅይታደል ወደኋላ የመለሰውን ኳስ አንተነህ መሳ በእጁ በመያዙ ሁለተኛ ቅጣት ምት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተሰጥቷል፡፡
ጭማሪ ደቂቃ
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 5 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
85′ ምንተስኖት አዳነ ወጥቶ ጎድዊን ቺካ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ ከተማ
80′ ተሾመ ታደሰ ወጥቶ ትርታዬ ደመቀ ገብቷል፡፡
* ከግቡ መቆጠር በኋላ በካታንጋ መቀመጫ በኩል ግርግር ተከስቷል፡፡ ድንጋይ ውርወራዎችም እየታዩ ነው፡፡
ጎልልል!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
77′ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ደጉ ደበበ በግንባሩ ገጭቶ ከመረብ አሳርፏል፡፡ 1-1
75′ እንዳለ ከበደ ሁለት የጊዮርጊስ ተከላካዮችን አልፎ ያቀበለውን ጣጣውን የጨረሰ ኳስ አመለ ሚልኪያስ ለማመን በሚከብድ ሁኔታ ሳይነካው አምልጦታል፡፡
ቢጫ ካርድ
72′ ፀጋዬ አበራ በሃይሉ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
68′ በሃይሉ ያሻገረውን ኳስ ምንተስኖት በግንባሩ ገጭቶ ቢሞክርም የግቡን አግዳሚ ገጭቶ ወጥቷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተደጋጋሚ ጫናዎች በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡
66′ ከማዕዘን የተሻማው ኳስ ሲመለስ በሃይሉ አግኝቶ ቢመታውም በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
65′ አበባው ቡታቆ የመታውን ቅጣት ምት አንተነህ መሳ አውጥቶታል፡፡ አደገኛ ሙከራ ነበር፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
61′ ናትናኤል ዘለቀ ወጥቶ ራምኬል ሎክ ገብቷል፡፡
ቢጫ ካርድ – አርባምንጭ
54′ ምንተስኖት አበራ በናትናኤል ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ቢጫ ካርድ – አርባምንጭ
52′ እንዳለ ከበደ ፊሽካ ከተነፋ በኋላ ኳስ አላግባብ በማቆየቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ቢጫ ካርድ – አርባምንጭ
51′ አመለ ሚልኪያስ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
50′ አዳነ ግርማ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጫና እየፈጠረ ይገኛል፡፡
46′ ከምንተስኖት የተሻገረለትን ኳስ አዳነ ግርማ ሞክሮ አንተነህ መሳ በግሩም ቅልጥፍና ወደ ውጪ አውጥቶበታል፡፡
ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ
የእረፍት ሰአት ለውጥ
አንዳርጋቸው ይላቅ ወጥቶ መሃሪ መና ገብቷል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በአርባምንጭ መሪነት ተጠናቋል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ጎልልል!!! አርባምንጭ
36′ ተሾመ ታደሰ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት አርባምንጭ ከተማን መሪ አድርጓል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ ከተማ
28′ በረከት ቦጋለ (ጉዳት) ወጥቶ ምንተስኖት አበራ ገብቷል፡፡
27′ ታደለ መንገሻ መሬት ለመሬት የሞከረው ኳስ በግቡ ቋሚ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
24′ አዳነ ግርማ ሰጥን ውስጥ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ላይ ወጥቷል፡፡
22′ አበባው ቡታቆ የመታው ቅጣት ምት የግቡን አግዳሚ ሲመልስ በሃይሉ በግንባሩ ገጭቶ ሞክሮ በድጋሚ አግዳሚውን ገጭቶ ተመልሷል፡፡
17′ አበባው ቡታቆ የመታው ቅጣተት ምት ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
13′ ምንያህል ከግራ መስመር ያሻገረውን ኳስ በሃይሉ በቮሊ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
10′ ጨዋታው በመሃል ሜዳ እንቅስቃሴ የተገደበ ነው፡፡ የግብ ሙከራ እስካሁን አልተደረገም፡፡
ተጀመረ
ጨዋታው በአርባምንጭ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
22 ዘሪሁን ታደለ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 15 አስቻለው ታመነ – 4 አበባው ቡታቆ
26 ናትናኤል ዘለቀ – 21 ተስፋዬ አለባቸው – 23 ምንተስኖት አዳነ
ምንያህል ተሾመ – 19 አዳነ ግርማ – 7 በሃይሉ አሰፋ
ተጠባባቂዎች
30 ሮበርት ኦዶንካራ
14 አለማየሁ ሙለታ
3 መሃሪ መና
5 አይዛክ ኢዜንዴ
20 ዘካርያስ ቱጂ
17 ራምኬል ሎክ
16 ጎድዊን ቺካ
የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ
1 አንተነህ መሳ
2 ወርቅይታደል አበበ – 16 በረከት ቦጋለ – 4 አበበ ጥላሁን – 13 ፀጋዬ አበራ
7 እንዳለ ከበደ – 18 አማኑኤል ጎበና – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 17 ታደለ መንገሻ
11 አመለ ሚልኪያስ – 23 ተሾመ ታደሰ
ተጠባባቂዎች
60 መሳይ አያኖ
3 ታገል አበበ
8 ትርታዬ ደመቀ
21 ምንተስኖት አበራ
6 ታሪኩ ጎጀሌ
14 አብዮት ወንድይፍራው
20 አብይ በየነ