አዲስ አበባ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

አዲስ አበባ ከተማ1-2ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ጨዋታው በንግድ ባንክ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ክለብም በያዝነው የውድድር ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ 3 ነጥብ ማግኘት ችሏል።



90′ ጎል!!!

ሳሙኤል ዮሐንስ ከቢንያም ሲራጅ በረጅሙ የተሻገረውን ኳስ ወደግብ በመቀየር ንግድ ባንክን መሪ አድርጓል።


90′ ተጨማሪ ሰዓት – 5 ደቂቃ


80′ ጎል!!!

ፒተር ኑዋዲኬ ፍፁም ቅጣት ምቱን በአግባቡ በመጠቀም ንግድ ባንክን አቻ አድርጓል።


79′ ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ በፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ላይ በሰራው ጥፋት ምክኒያት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝቷል።


77′ ጎል!!!

ዘሪሁን ብርሀኑ ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ አክርሮ የመታው ኳስ ግብ ሆኗል። አዲስ አበባ ከተማም ጨዋታውን መምራት ጀምሯል።


64′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ታዲዮስ ወልዴ ወጥቶ አምሀ በለጠ ገብቷል።


61′ የተጫዋች ለውጥ – አዲስ አበባ ከተማ

መሀጅር መኪ ወጥቶ ፀጋ አለማየሁ ገብቷል።


57′ ፒተር ኑዋዲኬ ያሻማው የማዕዘን ምት በቀጥታ ግብ ከመሆን በግብ ጠባቂው ጥረት ከሽፏል።


55′ ዳዊት ማሞ በግምት ከ25 ሜትር ርቀት ወደግብ የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።


46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል።



የመጀመሪያው አጋማሽ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።


45′ ተጨማሪ ሰዓት – 1 ደቂቃ


44′ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ከቢንያም የተሻገረለትን ኳስ ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል።


42′ ምንያምር ጴጥሮስ በቀኝ በኩል አክርሮ የመታው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።


39′ ዮናታን ብርሃነ አስመስሎ ወድቋል በሚል የጨዋታውን ሁለተኛ ቢጫ ካርድ አይቷል።


36′ ታዲዎስ ወልዴ ከሳጥኑ መሀል ወደግብ የመታው ኳስ ዒላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል።


29′ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ከሳጥኑ ውጪ በአየር ላይ እንዳለ የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።


23′ አዲሱ ሰይፉ ያገኘውን ወርቃማ ዕድል ኳሱን መቆጣጠር ባለመቻሉ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።


14′ ዳዊት ማሞ እጁን በመጠቀም ግብ ለማስቆጠር በመሞከሩ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።


8′ ፍቃዱ አለሙ ከሳጥኑ ውጪ ወደግብ አክርሮ ቢመታም ግብ ጠባቂው አውጥቶታል።


3′ ታዲዮስ ወልዴ ወደግብ የመታውን ኳስ የግቡ ቋሚ መልሶታል።


2′ ፍቃዱ አለሙ ከሰይፈ መገርሳ የተሻገረለትን ኳስ በደረቱ ተቆጣጥሮ ቢመታም ከዒላማ ውጪ ሆኗል።


1′ ጨዋታው በንግድ ባንክ አማካኝነት ተጀምሯል።


ከ1977 እስከ 1981 ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጫወተው እና በዚህ ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ዘላለም ተሾመ እንደ ትናንትናው ዛሬም የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።



አሰላለፍ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1 – ኢማኑኤል ፌቦ

15 አዲሱ ሰይፋ – 12 አቤል አበበ – 16 ቢኒያም ሲራጅ – 13 አንተነህ ገብረክርስቶስ 

2 ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን – 88 ታዲዮስ ወልዴ – 4 ጅብሪል አህመድ – 21 ዮናስ ገረመው- 80 ቢኒያም በላይ

11 ፒተር ንዋድኬ

ተጠባባቂዎች

29 ሙሴ ገብረኪዳን 

7 ዳንኤል አድሀኖም 

6 አመሀ በለጠ

44 ሳሙኤል ዮሀንስ 

99 ዳንኤል ለታ

10 ዳኛቸው በቀለ

5 ቶክ ጀምስ


አሰላለፍ – አዲስ አበባ ከተማ 

1 ተክለማርያም ሻንቆ

7 ምንያምር ጲጥሮስ – 20 ሰይፈ መገርሳ – 70 ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ – 77 አማረ በቀለ

40 ዳዊት ማሞ – 13 ዘሪሁን ብርሃኑ – 30 መሀጅር መኪ- 90 አቤል ዘውዱ – 10 ዮናታን ብርሃነ

24 ፍቃዱ አለሙ 

ተጠባባቂዎች 

99 ዳንኤል ተሾመ

81 አለማየሁ ሙለታ

6 ጊት ጋትኮች

80 አዳነ በላይነህ 

83 ፀጋ አለማየሁ 

8 ኤፍሬም ቀሬ

60 እሱባለው ሙሉጌታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *