መከላከያ ከ አዲስ አበባ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTመከላከያ   2-1  አአ ከተማ

1′ ኃይሌ እሸቱ | 40′ ሳሙኤል ታዬ 47′ ምንይሉ ወንድሙ


ተጠናቀቀ !!!

ጨዋታው በመከላከያ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ጦሩ 4ኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
90+2′ ምንይሉ ወንድሙ ወጥቶ መስፍን ኪዳኔ ገብቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 5

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
85′ ሳሙኤል ታዬ ወጥቶ ቴዎድሮስ ታፈሰ ገብቷል፡፡

81′ ቴዎድሮስ በቀለ ተከላካዮችን አልፎ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ከተገናኘ በኀላ የመታው ኳስ ቋሚውን ገጭቶ ተመልሷል፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!

የተጫዋች ለውጥ – አአ ከተማ
77′ ዮናታን ብርሃነ ወጥቶ ኤፍሬም ቀሬ ገብቷል፡፡

74′ ቴዎድሮስ በቀለ ከግብ ጠባቂው ጋር ያገናኘውኝ ኳስ ምንይሉ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

72′ ሳሙኤል ሳሊሶ ተከላካዮችን አልፎ ከሳጥን ውጪ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ደረጄ አድኖታል፡፡

59′ እንየው ካሳሁን ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አቤል ዘውዱ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

49′ ኃይሌ አሸቱ ከሳጥኑ የቀኝ ጠርዝ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

ጎልልል!!!! መከላከያ
47′ ቴዎድሮስ በቀለ በግራ በኩል የግል ጥረቱን ተጠቅሞ ይዞ በመግባት ያሻማውን ኳስ ምንይሉ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

46′ ሚካኤል ደስታ በግንባሩ ገጭቶ የሞከረውን ኳስ ደረጄ ይዞበታል፡፡


እረፍት !
የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ጎልልል!!!! መከላከያ
40′ ሳሙኤል ታዬ ከማራኪ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ መከላየከያን አቻ አድርጓል፡፡

37′ አቤል ዘውዴ በግሩም ሁኔታ በቮሊ የመታው ኳስ በግቡ ቋሚ ለጥቂት ወጥቷል፡፡

28′ ጨዋታው ፈጣን እንቅስቃሴ እየታየበት ቢገኝም በሁለቱም በኩል ከመሃል ሜዳ የዘለለ እንቅስቃሴ እየታየ አይደለም፡፡

14′ ዘሪሁን ብርሃኑ ከቅጣት ምት የሞከረውን ኳስ አቤል ይዞበታል፡፡

10′ ማራኪ ወርቁ ከርቀት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

7′ አቤል ዘውዱ ከርቀት የሞከረውን ኳስ አቤል ይዞበታል፡፡

ጎልልል!!!! አዲስ አበባ ከተማ
ኃይሌ እሸቱ የውድድር ዘመኑን ፈጣን ግብ በ29ኛው ሴኮንድ በማስቆጠር አአ ከተማን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

ተጀመረ!!
ጨዋታው በአአ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

የመከላከያ አሰላለፍ

1 አቤል ማሞ

3 ቴዎድሮስ በቀለ — 16 አዲሱ ተስፋዬ — 4 አወል አብደላህ — 2 ሽመልስ ተገኝ

19 ሳሙኤል ታዬ — 21 በሀይሉ ግርማ — 13 ሚካኤል ደስታ — 9 ሳሙኤል ሳሊሶ

7 ማራኪ ወርቁ — 14 ምንይሉ ወንድሙ

ተጠባባቂዎች

22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
28 ሚሊዬን በየነ
17 ምንተስኖት ከበደ
11 ካርሎስ ዳምጠው
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
10 የተሻ ግዛው
23 መስፍን ኪዳኔ

የአዲስ አበባ ከተማ አሰላለፍ

98 ደረጀ ዓለሙ

2 እንየው ካሳሁን – 20 ሰይፈ መገርሳ – 70 ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ – 77 አማረ በቀለ

40 ዳዊት ማሞ – 13 ዘሪሁን ብርሃኑ – 83 ፀጋ አለማየሁ – 90 አቤል ዘውዱ – 10 ዮናታን ብርሃነ

8 ኃይሌ እሸቱ

ተጠባባቂዎች

1 ተክለማርያም ሻንቆ
7 ምንያምር ጴጥሮስ
81 አለማየሁ ሙለታ
6 ጊት ጋትኮች
53 ኤፍሬም ቀሬ
80 አዳነ በላይነህ
20 እሱባለው ሙሉጌታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *