ተክለወልድ ፍቃዱ በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ

 

የመከላከያው ድንቅ አማካይ ተክለወልድ ፍቃዱ ከቢሾፍቱ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በደረሰበት የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፡፡ በአደጋው የተክለወልድ ወንድም አብሮት የነበረ ሲሆን እሱም ህይወቱ አልፏል፡፡

አደጋው ሲደርስ በቦታው የነበረ ያሬድ የተባለ የአይን እማኝ ለኤፍኤም 97.1 የተናገረው እንዲህ ባለ መልኩ ነበር ‹‹ አደጋው የደረሰው ትላንት ከምሽቱ 2፡00 አካባቢ ነበር፡፡ በመኪናው ውስጥ 5 ሰዎች የነበሩ ሲሆን ተክለወልድ እና ወንድሙ ጋቢና ውስጥ ነበሩ፡፡ መኪናው መንገዱን ስቶ ከግንድ ጋር ሲላተም ጋቢና የነበሩት ወንድማማቾች ወድያው ሲሞቱ ከኋላ ተቀምጦ የነበረው አንደኛው እግሩ ተቆርጧል፡፡ ›› ሲል ስለ አደጋው አብራርቷል፡፡

የ24 አመቱ የቀድሞው የአየር ኃይል አማካይ በቅርብ አመታት ከታዩ ባለ ድንቅ ክህሎት አማካዮች አንዱ የነበረ ሲሆን በመልካም ባህርዩ በርካቶች የሚያወድሱት ድንቅ ተጫዋች ነበር፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ ለቤተሰቦቹ ፣ ለአድናቂዎቹ እና ለመከላከያ ስፖርት ክለብ አባላት መፅናናትን ትመኛለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *