ሲዳማ ቡና ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር የተለያየው አማካዩ ኃይለየሱስ መልካን አስፈርሟል፡፡ ኃይለየሱስ የይርጋለሙን ክለብ ያስፈረሙት እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ በሚቆይ ውል ነው፡፡
ኃይለየሱስ አዲስ አበባ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ከረዱት ተጫዋቾቸች አንዱ የነበረ ሲሆን በክለቡ የፕሪምየር ሊግ ታሪክ የመጀመርያውን ጎል ማስቆጠርም ችሎ ነበር፡፡ ሆኖም ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ከክለቡ ጋር ባለመስማማት መለያየቱ ይታወሳል፡፡