የዘንድሮ ሲቲ ካፕ ውድድሮች መቼ ይደረጋሉ?

ክለቦች ወደ አዲስ አመት የሊግ ውድድር ከመግባታቸው አስቀድሞ የቡድናቸውን አቋም ለመገምገም እንደ አቋም መፈተሻ ጨዋታ እየተጠቀሙበት የሚገኙት በተለያዩ ከተሞች የሚዘጋጁ የሲቲ ካፕ ውድድሮች ናቸው። ከወራት ቆይታ በኋላ ውድድሮችን ከመከታተል ለራቀው የስፖርት ቤተሰብ እንደ ጥሩ የመዝናኛ እና የሚደግፉት ቡድን ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለማወቅ እንደ አንድ አጋጣሚ እየወሰዱት የሚገኘው እነዚህ ውድድሮች አዘጋጅ አካላት ከስፖንሰር ፣ ከተመልካች ገቢ ከፍተኛ ተጠቃሚ እየሆኑ የሚገኙባቸው እነዚሀ ውድድሮች ዘንድሮም እንደ ወትሮ ሁሉ ከመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች በድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ

ከመስከረም 20 – ጥቅምት 4 ቀን በስምንት ቡድኖች መካከል ለማድረግ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳዘጋጀ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል። የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቀድሞ ካወጣው መርሐ ግብር ጋር እንዳይጋጭ የአዲስ አበባ ኳስ ፌዴሬሽን የፕሮግራም ማስተካከያ እንዲያደርግ ደብዳቤ እንዳስገባም ሰምተናል። የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከመቼውም አመታት በተሻለ ዘንድሮ ጠንካራ ውድድር ለማዘጋጀት እንዳሰበና የክልሉ የፕሪምየር ሊግ ቡድኖች እና ተጋባዥ ቡድኖች በውድድሩ ላይ እንደሚካፈሉ ታውቋል።

የደቡብ ዋንጫ

ከመስከረም 7 አንስቶ በስምንት ቡድኖች መካከል ውድድሩን ለማዘጋጀት የደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅድመ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ እንዲሁም በውድድሩ ላይ እንዲጋበዙ ላሰቧቸው ተጋባዥ ክለቦች ለቀረበው የተሳትፎ ግብዣ መልስ እየጠበቁ እንደሆነና ምላሻቸው እንደታወቀ ውድድሩ እንደሚጀመር ፣ የምድብ ድልድሉም በቅርብ በቀናት እንደሚገለፅ ሰምተናል።

ከዚህ ውጭ የውድድሩ የመጀመርበት ቀን እና ቦታ አይታወቅ እንጂ የትግራይ ክልል ፣ የአማራ ክልል ፣ የኦሮሚያ ክልል የዋንጫ ውድድሮች በፕሪምየር ሊግ በሚወክሏቸው ክለቦች ፣ በከፍተኛ ሊግ በሚሳተፉ ክለቦች እና በተጨማሪ ተጋባዦች በሁለት ምድብ የተከፈለ ውድድር ከመስከረም ወር መጀመርያ አንስቶ እንደሚያዘጋጁ አወቀናል ።

ሶከር ኢትዮዽያ በቀጣዮቹ ቀናት ከውድድሮቹ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ መረጃዎችን ተከታትላ ወደ እናተ የምታቀርብ እንደሆነ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *