ዋልያዎቹ ዛሬ ማታ አዲስ አበባ ይገባሉ

ትናንት በአራተኛ የምድብ ጨዋታ በናይሮቢው ካሳራኒ ስታድየም በኬንያ የ3-0 ሽንፈት የደረሰበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ማምሻውን አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

ወደ 2019 የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ለማቅናት ትናንት አራተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ዋልያዎቹ ውጤት ሳይቀናቸው መቅረቱ ይታወሳል። ነገር ግን ድል አድርገው ይመለሱ የነበረ ቢሆን የቡድኑ ተጨዋቾች በነፍስወከፍ የ30,000.00 ብር ማበረታቻ ሊሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸው እንደነበር ተስምቷል። በተጨማሪም የቡድኑ አባላት ከኬንያ በመነሳት ዛሬ ምሽት 1፡00 ላይ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የታወቀ ሲሆን አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በቅርቡ ጨዋታውን የተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡም ይጠበቃል።