ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት የሚያደርጉት ጨዋታ ላይካሄድ ይችላል

በ17ኛ ሳምንት ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት ጨዋታ አስቀድሞ በወጣለት መርሐ ግብር መሠረት ላይካሄድ ይችላል።

መጋቢት 15 እሁድ 10:00 ላይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው አጋማሽ የውድድር ዘመን 17ኛ ሳምንት ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት ጨዋታቸውን እንዲያደርጉ አስቀድሞ መርሐ ግብር ማውጣቱ ይታወሳል። ሆኖም በኢትዮጵያ ቡና በኩል በአሁኑ ሰዓት አማኑኤል ዮሐንስ እና አቡበከር ናስር ለ23 ዓመት በታች የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን ምክንያት ለኢትዮጵያ ቡና አገልግሎት እየሰጡ አይገኙም። አሁን ደግሞ ብሩንዲያዊ አዲስ ፈራሚ አጥቂ ሐሰን ሻባኒ ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ለመጫወት ጥሪ ቀርቦለት ወደ ሀገሩ ሲያቀና ሌላው ዩጋንዳዊው አማካይ ክሪዚስቶም ንታምቢ በተመሳሳይ ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት ለመጫወት ወደ ሀገሩ አምርቷል።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ደንብ መሠረት አንድ ቡድን ሦስት ወይም ከሦስት በላይ ለብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ካስመረጠ ውድድር እንደማያደርግ የተቀመጠ በመሆኑ አወዳዳሪው አካል በቅርቡ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚያሳውቀው ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ቡና እና የደደቢት ጨዋታ ወደ ሌላ ቀን የመተላለፍ ዕድል ሰፊ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *