U-20 | አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ ረዳቶቻቸውን አሳወቁ

በአስመራ የሚካሄደው “የሠላም እና ወዳጅነት ዋንጫ” ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን እንዲያሰለጥኑ በትናንትናው ዕለት የተመረጡት አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ ረዳቶቻቸውን አሳወቁ።

በሚያዚያ ወር መጀመርያ በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ አዘጋጇን ሀገር ጨምሮ ጅቡቲ ፣ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የሚካፈሉበት “የሠላም እና ወዳጅነት ከ20 ዓመት በታች ውድድር” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ለመቅጠር ፌዴሬሽኑ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከተወዳደሩት እጩዎች መካከል የተሻለ ድምፅ በማግኘት በትናትናው ዕለት አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬን ለዋና አሰልጣኝነት መምረጡ ይታወሳል።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

አሰልጣኝ ዮሴፍ ዛሬ አብረዋቸው የሚሰሩትን የቡድን ረዳቶቻቸውን ያሳወቁ ሲሆን በዚህም መሠረት ምክትል አሰልጣኝ በማድረግ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሰበታ ከተማ በተከላካይ ስፍራ የተጫወተውን እና ያለፉትን ሦስት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ከ17 ዓመት በታች አሰልጣኝ በመሆን ስኬታማ ስራ እየሰራ የሚገኘውን ብርሃኑ ወርቁን ሲመርጥ፤ የግብጠባቂ አሰልጣኝ በማድረግ ደግሞ የቀድሞ የወላይታ ቱሳ፣ ሀላባ ከተማ፣ ፔፕሲ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂነበረውና በአሁኑ ወቅት የወላይታ ድቻ ከ20 ዓመት በታች ቡድንን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ በመሆን እያገለገለ የሚገኘው ዘላለም ማትዮስን ምርጫቸው አድርገዋል።

በቀጣይ ከውድድሩ ቀን መቃረብ ምክንያት በፍጥነት ተጫዋቾችን በመጥራት ለተወሰኑ ቀናት የምልመላ ስራዎችን ከሰሩ በኋላ ወደ አስመራ የሚያቀኑትን 23 ተጫዋቾችን ለይተው ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *