የዲሲፕሊን ኮሚቴ በረከት ሳሙኤል ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ

በተስተካካይ መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና ባካሄዱት ጨዋታ የውድድር ታዛቢው ባቀረቡት ሪፖርት መነሻነት ያልተገባ ድርጊት ፈፅሟል በሚል የዲሲፒሊን ኮሚቴ በረከት ሳሙኤል ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ።

ሐሙስ የካቲት 14 በአንጋፋው የድሬዳዋ ስታዲየም በተስተካካይ መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና የተካሄደው ጨዋታ በሲዳማ ቡና 3-1 በሆነ ውጤት አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወቃል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በረከት ሳሙኤል እና ግርማ በቀለ የፈጠሩት አለመግባባትን ተከትሎ የፊት ጥርሱ የወለቀው ግርማ በቀለ ሜዳው ላይ የወለቀ ጥርሱን በማሳየት በረከት ሳሙኤል እንደመታው በእንባ ለዕለቱ ዳኞች እና ኮሚሽነሩ ቅሬታውን ሲያቀርብ እንደነበረ መዘገባችን የሚታወስ ነው።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

የዲሲፕሊን ኮሚቴው የጨዋታው ታዛቢ ያቀረቡትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ በረከት ሳሙኤል ላይ የአምስት ጨዋታ ቅጣት እና ግርማ በቀለ በሚያቀርበው የህክምና ሰነድ መሰረት ሙሉ የህክምና ወጪውን እንዲከፍል ውሳኔ አስተላልፎበታል።

የድሬዳዋ ተከማ እግርኳስ ክለብ በውሳኔው ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳደረበት በመግለፅ ለፌዴሬሽኑ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ጉዳዩ በገደብ ተይዞ እስኪታይ ድረስ በቀጣይ ጨዋታዎች በረከት ሳሙኤል ሊጫወት እንደሚችል ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *