በሊጉ እጣ ፈንታ ዙርያ ፌዴሬሽኑ ስብሰባ ተቀምጧል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተያዘላቸው መርሐ ግብር ይካሄዳሉ ያለው ፌዴሬሽኑ በአሁኑ ሰዓት ስብሰባ መቀመጡ ታውቋል።

የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ በስብሰባው የቅዱስ ጊዮርጊስ የትላንት መግለጫ እንዲሁም የመቐለ እና ሲዳማ ቡና ቅሬታን በማንሳት እንደሚወያይ የሚጠበቅ ሲሆን የሊጉ በተለይም የዛሬ ጨዋታዎች እጣ ፈንታ ላይ አንዳች ውሳኔ ወስኖ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የ29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ ተብለው መርሐ ግብር እንደወጣላቸው የሚታወስ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ “ተስተካካይ ጨዋታ ሳላከናውን ወደ ጎንደር አላመራም” ማለቱ፤ ሲዳማ ቡና እና መቐለም በጉዳዩ ዙርያ ያላቸውን አቋም ለፌዴሬሽኑ መግለፃቸው ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡