የስፖርት ጋዜጠኛ ምስጋናው ታደሰ በጠና ታሟል

በኤሌክትሮኒክስ እና ህትመት ሚዲያዎች ያለፉትን 20 ዓመታት በስፖርት ጋዜጠኝነት ስማቸው ጎልቶ ከሚጠሩት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው ምስጋናው ታደሰ በእግሩ ላይ ከፍተኛ ህመም አጋጥሞታል።

የጋዜጠኛው ጉዳት መነሻ በመኖሪያ ቤቱ በራፍ ላይ አዳልጦት ከወደቀና የደረጃ መወጣጫ ከመታው በኋላ ነው። በወቅቱ ለጉዳቱ ብዙም ትኩረት ሳይሰጠው በቸልታ ቢያልፈውም ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን የቀኝ እግሩ ከጉልበቱ በታች በፍጥነት በማበጡ ከእንቅስቃሴ ሊያግደው ችሉዋል። ያለፉትን ቀናትም ከሚወደው ሙያ ርቆ በህክምናና በአልጋ ላይ ለማሳለፍ ተገዷል። በህመሙ ከተረታበት ቀን አንስቶ ራሱን ችሎ መራመድ ስለማይችል እያንዳንዷን እንቅስቃሴ የሚያደርገው በሰዎች ድጋፍ ነው። በተለይም የቅርብ ወዳጁ አቶ ሰሎሞን ኃ/ሚካኤል በዚህ ረገድ ከአጠገቡ ባለመራቅ ከፍተኛ እገዛ እያደረጉለት እንደሚገኝ ለሶከር ኢትዮጵያ ይህን ተናግሯል።

” ባለፈው ሳምንት ያጋጠመኝን ጉዳት ቀለል አድርጌ ችላ ብለውም ከቀናት ወዲህ ግን እየባሰብኝ መጣ። ለህክምና ያመራሁበት ሆስፒታል ጉዳቴን ሲያዩ በጣም ነው የደነገጡት። ችላ ብዬ በመቆየቴ ከወቀሰችኝ በሁዋላ ህክምናዬን ተከታትዬ ስጨርስ ‘አሁን የምልህን መምሪያ በጥንቃቄ አድምጠኝ። መድኃኒቶቹ ፈዋሽ የመሆናቸውን ያህል መርዛማም ናቸው። ከዚህ ውስጥ አንዱን ለአንድ ቀን ብታጉዋድል ጉዳትህ ወደ ሰውነትህ በፍጥነት ተሰራጭቶ ቀኝ እግርህን ከጉልበትህ በታች ትቆረጣለህ’ የሚል አስደንጋጭ ነገር ሰምቻለው።

” ህክምናዬን በአግባቡ እየተከታተልኩ እገኛለው። ኢንፌክሽኑ ወደ ሌሎች የቀኝ እግሬ አካላት እየተስፋፋ መሆኑን ዶክተሮቹ ነግረውኛል። ከዚህ በኋላ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፤ በቀጣይ ቀጠሮዬ ሁሉን ነገር አውቃለው። ለተሻለ ህክምና ከሀገር ውጭ ታክሜ እና ሙሉ ጤንነቴ ተመልሶ ወደምወደው ሙያ መመለስን ስለምፈልግ ስፖርት ወዳዱ የሀገሬ ሰው አቅሙ በፈቀደ መጠን ድጋፍ እንዲያደርግልኝ እጠይቃለው።” ብሏል።

ጋዜጠኛ ምስጋናው ታደሰን ለመደገፍ በብስራት ሬድዮ መስራች እና ባለቤት በጋዜጠኛ መሰለ መንግስቱ፣ የቅርብ ወዳጁ ሰሎሞን ኃ/ሚካኤል እና የሙያ ባልደረባው ታደለ አሰፋ የሚመራ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን ምስጋናውን መርዳት እና መደገፍ የሚፈልግ አካል

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ1000268456639

አዋሽ ባንክ 01320148371700


© ሶከር ኢትዮጵያ