ባህር ዳር ከተማ ተጫዋች ማስፈረሙን ቀጥሏል

በርካታ ተጨዋቾችን ወደ ቡድናቸው በመቀላቀል የቅድመ ውድድር ልምምዳቸውን በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም እያደረጉ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች ከቀናት በፊት ወደ ቡድናቸው ቀላቅለው ልምምድ ሲያሰሩት የነበረውን ሳምሶን ጥላሁን አስፈርመዋል።

በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ያደገው እና አንድ ዓመት በቡድኑ ተጫውቶ ያሳለፈው ሳምሶን በ2006 ክለቡን ለቆ ወደ ደደቢት ማምራቱ ይታወሳል። በደደቢት ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ በ2010 ወደ ኢትዮጵያ ቡና ያመራው ተጨዋቹ አሁን ለሁለት ዓመታት በባህር ዳር ለመቆየት ተስማምቶ ፊርማውን አኑሯል።

ባህር ዳር በቅርቡ ሌላው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አፈወርቅ ኃይሉን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሶ ሳይፈርም መቅረቱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ