ዩጋንዳ ኤርትራን በማሸነፍ የሴካፋ ዋንጫን ለአስራ አምስተኛ ጊዜ አሸነፈች

ዛሬ በተካሄደው የሴካፋ ዋንጫ ፍፃማ ዩጋንዳ አስደናቂ ጉዞ ያደረገችው ኤርትራን 3-0 በማሸነፍ የሴካፋ ዋንጫ አነሳች።

ላለፉት ሳምንታት በዩጋንዳ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየውና ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችበት የሴካፋ ዋንጫ በዩጋንዳ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ሳይጠበቁ ለፍፃሜ የደረሱት የቀይ ባሕር ግመሎች እና ክሬኖቹን ያገናኘውን ይህ ጨዋታ ዩጋንዳ በብራይት አንኳኒ፣ ሙስጠፋ ኪዛ እና ጃኦል ማዶንዶ ተጋጣሚዋን አሸንፋ የውድድሩን ዋንጫ ለ15 ጊዜ አንስታለች።

የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች የኤርትራው ሮቤል ተክለሚካኤል ሆኖ ሲሸለም በርካታ የኤርትራ ተጫዋቾችም ስማቸው ከተለያዩ ክለቦች መያያዝ ጀምሯል። ከወዲሁም በውድድሩ ጥሩ ብቃቱን ያሳየው እና የበርካቶች ቀልብ የሳበው ሮቤል ተክለማርያም ከታንዛንያው ክለብ ያንጋ አመራሮች ጋር ንግግር መጀመሩ ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ወደ ስፍራው ያቀናው ጋዜጠኛ ገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ