ፋሲል ከነማ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል

ፋሲል ከነማ እና የደጋፊ ማኅበሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የሚውል የ360 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

በኮሮና ቮይረስ ወረርሽኝ አማካኝነት ለሚፈጠረው ችግር ክለቦች እና አጠቃላይ የስፖርት ቤተሰቡ ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ፋሲል ከነማ እግርኳስ ክለብም የበኩሉን ድጋፍ አድርጓል። የፋሲል ከነማ ዋናው እና የታዳጊ ቡድን ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና አጠቃላይ አባላት 260,000 ብር፣ የደጋፊ ማኅበሩ 100,000 ብር በአጠቃላይ 360,000 ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን የኮሮና ቮይረስ ስርጭትን ለመግታት ለሚደረገው ርብርብ በቀጣይም መሰል ድጋፎች እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ