የታሰሩት ተጫዋቾች ጉዳይ…

የሾኔ ባድዋቾ ከተማ ተጫዋቾች ደመወዝ ለመጠየቅ ወደ ቢሮ በሚሄዱበት ሰዓት ለእስር መዳረጋቸው ከሰሞኑ በአብይ ርዕስነት በበርካቶች ዘንድ ትኩረትን ያገኘ ዜና ሆኗል።

በሣምንቱ አጋማሽ ነበር አስር ቡድኖችን አቅፎ በሚገኘው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ረ ላይ በዘጠኝ ነጥቦች በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ የሚገኘው የሾኔ ባድዋቾ ከተማ ተጫዋቾች የአምስት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም በሚል በተደጋጋሚ ለክለቡ በደብዳቤ ቅሬታ ቢያቀርቡም አጥጋቢ ምላሽ በማጣታቸው ወደ ክለቡ ያቀኑት። በወቅቱም ስምንት የሚሆኑ ተጫዋቾች አቤቱታቸውን ያሰሙ ሲሆን ጉዳያቸው ምላሽ ከማግኘቱ በፊትም ለእስር መዳረጋቸው ታሰምቷል፡፡ ተጫዋቾቹ ለምን መብታቸው ለመጠየቅ በሄዱበት ወቅት ለእስር ተዳረጉ ? ወይንስ ያጠፉትን ሊያሳስራቸው የሚችል ጉዳይ ነበር ? ለሚሉት ጥያቄዎች የክለቡ የቡድን መሪ አቶ ዳዊት ዴሞን ለሶከር ኢትዮጵያ ተካታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ተጫዋቾቹ በወቅቱ ደመወዛቸውን ለመጠየቅ ወደ ፋይናስ ሄደው ነበር። ሲሄዱ ግን አላስፈላጊ ቃላትን ተናግረዋል ፤ የፋይናንስ ኃላፊዋንም ተስድበዋል። እሷም መሰደቧን ለማናጅመንት አሳውቃ ክስ ተመስርቶ ለአንድ ቀን ከታሰሩ በኃላ በዋስ ወጥተዋል። እንደ ከተማ የካሽ እጥረት ስለነበረ በአግባቡ መክፈል አልቻልንም። ያን ተከትሎ ነው ተጫዋቾቹ አላስፈላጊ ቃል ሊወረውሩ የቻሉት። እኛ እንደ ክለብ ጉዳዩን ለማስፈፀም እየሰራን ነው። እነሱ የሄዱት ጉዳዩ ቶሎ ይፈታልናል ብለው ነበር ፤ ያ አልሆነም። ከአሁን በኃላ ግን ችግር ሳይፈጠር ጥያቄያቸው ለመፍታት ጥረት ላይ ነን”
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ