መከላከያ አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

በከፍተኛ ሊግ እየተወዳደረ የሚገኘው መከላከያ ዮሐንስ ሳህሌን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል።

ክለቡ በዚህ ሳምንት ከዘላለም ሽፈራው ጋር መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን አመራሮቹ ቀጣዩን አሰልጣኝ ለመቅጠር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተው ዮሐንስ ሳህሌን ምርጫቸው በማድረግ በአንድ ዓመት ውል አሰልጣኝ አድርገው ቀጥረዋል። ክለቡ አሰልጣኙን ለማስፈረም እስከ 2 ሚልየን ብር የሚደርስ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ሲነገር 80 ሺህ ብር ወርሐዊ ደሞዝ እንደሚከፍል ለማወቅ ተችሏል።

የቀድሞው የራስ ሆቴል እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበሩት ዮሐንስ ሳህሌ ከረጅም ዓመታት የአሜሪካ ኑሮ በኋላ በፌዴሬሽኑ እና ደደቢት ቴክኒክ ዳይሬክተርነት የሰሩ ሲሆን በመቀጠል በደደቢት (ሁለት ጊዜያት)፣ ብሔራዊ ቡድን፣ መቐለ 70 እንደርታ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ወልዋሎ መስራታቸው ይታወቃል።

በ2011 ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረደው መከላከያ ዘንድሮ የከፍተኛ ሊጉ ውድድር ከኮሮና ወረርሺኝ ምክንያት እስከተሰረዘበት ድረስ በ11 ጨዋታዎች 18 ነጥቦችን በመሰብሰብ ከመሪው ነቀምቴ በ6 ነጥቦች ርቆ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ