ባህር ዳር ከተማ የግብ ጠባቂውን ውል አራዘመ

ከሰሞኑ የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም የተጠመዱት ባህር ዳር ከተማዎች ማምሻውን ደግሞ የፅዮን መርዕድን ውል አራዝመዋል፡፡

ከአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን 2008 ላይ ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ እስከ 2011 የውድድር ዘመን በመጫወት ያሳለፈው ይህ ግብ ጠባቂ በ2012 ባህር ዳር ከተማን ከተቀላቀለ በኃላ ከሀሪሰን ሄሱ ጋር በመፈራረቅ የክለቡን ግብ ጠብቋል። ይህ ወጣት ግብ ጠባቂ የአንድ ዓመት ውሉ በመጠናቀቁ ዛሬ ማምሻውን ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ቆይታን ለማድረግ ፊርማውን ለማኖር ተስማምቷል፡፡

ለቀጣዩ አመት የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ በፕሪምየር ሊጉ ለመቅረብ እየተሰናዱ ያሉት የጣና ሞገዶቹ እስከ አሁን ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ ውላቸው የታደሱ ተጫዋቾች ቁጥር አስራ አንድ ደርሷል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ