ሀዲያ ሆሳዕና አምስተኛ ተጫዋቹን አስፈረመ

የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሱሌይማን ሰሚድ አዳማን ለቆ ሀዲያ ሆሳዕናን የተቀላቀለ አምስተኛ ተጫዋች ሆኗል፡፡

በአንድ ዓመት ውል ነብሮቹን ለመቀላቀል የተስማማው የመሐል እና የመስመር ተከላካዩ ሱሌይማን ሰሚድ ከኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ የተገኘ ሲሆን በአዳማ ከተማ ላለፉት ሦስት ዓመታት መልካም ቆይታን ካደረገ በኋላ የቀድሞው አሰልጣኙን ፈለግ ተከትሎ ወደ ሆሳዕና አምርቷል፡፡

በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ መሪነት በዛሬው ዕለት አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ወደ ዝውውር ገበያው የገቡት ሀዲያ ሆሳዕናዎች እስካሁን አምስት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: