የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ድንገተኛ ስብሰባ ሊቀመጥ ነው

የእግርኳሱ የበላይ አካል የሆነው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ድንገተኛ ስብሰባ በቀጣዩ ሳምንት ሊያደርግ ነው።

የቀጣይ ዓመት ውድድር በሚጀመርበት ጉዳይ እና ውድድሩን ለማስጀመር ለመንግስት በቀረበው መነሻ ሀሳብ (ሰነድ) ዙርያ ያተኮረው የስብሰባው አጀንዳ የፊታችን ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን በ4:00 በፌዴሬሽኑ ፅሕፈት ቤት የሚካሄድ ይሆናል።

በዋናነት ከላይ ባነሳነው አጀንዳ ዙርያ በሚካሄደው የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ በአንዳንድ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ዘንድ በጉዳዩ ዙርያ አስቀድመው ምንም ዓይነት መረጃ ሳይኖራቸው ከሚዲያ መስማታቸውን ተከትሎ ሰነዱን ባዘጋጀው አካል ላይ ጠንከር ያለ ሀሳብ ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የ2013 ውድድር መቼ እንደሚጀምር ቁርጡ ባለየለት በዚህ ሰዓት ክለቦች በከፍተኛ ሁኔታ በዝውውሩ እየተሳተፉ ሲገኝ የማክሰኞው ስብሰባ ምንይዞ ይመጣል የሚለው ጉዳይም ተጠባቂ ነው።

በ2013 የውድድር ዘመን አካሄድ መነሻ ሀሳብ ዙርያ ያቀረብነው ዘገባ ፡- LINK


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ