የአሸናፊ በጋሻው የእውቅና መርሐግብር በቀጣይ ሳምንት ይደረጋል

ለቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና እና ለብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሸናፊ በጋሻው የተዘጋጀው የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም በቀጣይ ሳምንት በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ይካሄዳል።

በኢትዮጵያ ቡና የእግርኳስ ተጫዋችነቱን ጀምሮ በማድረግ በኢትዮጵያ ቡና ጫማውን የሰቀለው አስራ ሁለት ቁጥር ማልያ ለባሹ፣ ለአንድ ክለብ ታምኖ መጫወት እንደሚቻል በምሳሌነት ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው እና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከታዳጊ እስከ ዋና ቡድን ድረስ መጫወት ለቻለው ለአሸናፊ በጋሻው የተዘጋጀው የእውቅና መርሐ ግብር የፊታችን እሁድ ነሐሴ 24 ቀን ከምሽቱ 12:00 በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል እንደሚካሄድ ከአዘጋጅ ኮሚቴው መረጃ ደርሶናል።

በኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማኀበር በአስተባባሪነት እና የአሸናፊ በጋሻው ወዳጆች በተካፈሉበት በዚህ ፕሮግራም ላይ ሃምሳ የተመረጡ ግለሰቦች እንደሚታደሙበት፣ አሸናፊ በጋሻውን የሚያወሱ የተለያዩ ዝግጅቶች የሚቀርቡ እንደሆነ እና በመጨረሻም ለአሸናፊ ልዩ ስጦታ እንደሚበረከትለት ሰምተናል።

የቀድሞ ባለ ታሪክ እግርኳስ ተጫዋቾቻችን የምንዘክርበትእና እውቅና የምናቀርብበት መንገድ ብዙ ባልዳበረበት በዚህ ዘመን ለዚህ የቀድሞ ድንቅ ተጫዋች የታሰበውን የእውቅና ፕሮግራም ሌሎች ባለታሪኮቻችን በማስታወስ ተመሳሳይ ዝግጅቶች እንዲዘጋጁ የሚፈጥረው በጎ ተፅዕኖ ቀላል የሚባል አይደለም።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!