ሊግ ኩባንያው ከክለቦች ጋር ስብሰባ ተቀምጧል

የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል። ከዚህ መርሐግብር አስቀድሞ በአሁኑ ሰዓት የሊግ ኩባንያው በካፒታል ሆቴል ከክለቦች ጋር ስብሰባ ተቀምጧል።

በትናንትናው ዕለት ረጅም ሰዓት የፈጀ የውስጥ ስብሰባውን ያደረገው የፕሪምየር ሊጉ አወዳዳሪ አካል በዋናነት ከዲኤስ ቲቪ ጋር ተያይዞ የመጣው የልዑካን ቡድን መስተካከል ባለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ዙርያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከዛሬው የዕጣት ሥነ ስርዓት አስድሞ ከክለቦች ጋር በሚነጋገሩበት ጉዳዮች ዙርያ ምክክር አድርገዋል።

አሁን ረፋድ ላይ በዛው በካፒታል ሆቴል የአስራ ስድስቱም ክለብ አመራሮች ታድመውበታል በተባለው ስብሰባ የተለያዩ አጀንዳዎች ተነስተው ውይይት እያደረጉ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል። ምናልባትም በውድድሩ ጅማሮ ዙርያ እና በውድድሩ ደንብ ዙርያ አዳዲስ ነገሮች ይሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የ2013 የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት ዛሬ ከ08:00 ጀምሮ በካፒታል ሆቴል እንደሚካሄድ ሲታወቅ የዘንድሮው የውድድር ዓመት ታኅሣሥ 3 ጅማሮውን እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!