ዑመድ ኡኩሪ ወደ ሀገሩ ሊግ ይመለስ ይሆን ?

በሀገር ውስጥ ክለቦች፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በግብፅ ሊጎች ሲጫወት የምናውቀው ዑመድ ኡኩሪ ዳግም በሀገሩ ሊግ ሊጫወት ይችል ይሆን ?

የቀድሞው የመከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ኮከብ በ2006 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እና ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ካጠናቀቀ በኋላ ፈረሰኞቹን በመልቀቅ ወደ ግብፅ ሊግ አምርቶ አል-ኢትሀድ አሌክሳንድሪያ፣ ኤንፒ፣ ኤል-ኤንታግ ኤል-አርቢ፣ ስሞሀ እና አስዋን ክለቦች ሲጫወት መቆየቱ ይታወሳል።

በቅርቡ ወደ ሀገሩ የተመለሰው ዑመድ በፕሪምየር ሊጉ ክለቦች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። ምን አልባትም የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር በአዳማ ከተማ ልንመለከተው የምንችልበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ እየተነገረም ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ