ኢትዮጵያ ቡና ከ ፋሲል ከነማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ እና የውድድር ዘመኑን የቻምፒዮንነት ጉዞ ከሚወስኑ መርሐ ግብሮች አንዱ የሆነው የቡና እና ፋሲል ጨዋታ ወቅታዊ መረጀዎች እነሆ!

በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ተጋጣሚያቸውን እንደሚያከብሩ እና የእነርሱን አጨዋወት ገድቦ ጥሩ እንቅስቃሴ ለማድረግ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ የተናገሩት አሠልጣኝ ስዩም ከበደ ከአምስት ቀናት በፊት የዋንጫውን ሌላኛው ቀጥተኛ የዋንጫ ተፎካካሪ ቡድን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲያሸንፉ የተጠቀሙበትም ቋሚ አሰላለፍ ዛሬም ተጠቅመዋል።
አሠልጣኝ ካሳዬ አራጌ በበኩላቸው የዛሬው ጨዋታ ለዋንጫው ወሳኝ መሆኑን ተናግረው ከባለፈው የወልቂጤ ጨዋታ መጠነኛ ለውጦችን አድርገው ወደ ሜዳ እንደገቡ ገልፀዋል። በዚህም ኃይሌ ገብረትንሳይ ፣ምንተስኖት ከበደ እና እያሱ ታምሩን በአስራት ቱንጆ፣ ወንድሜነህ ደረጄ እና ዊሊያም ሰለሞን ተክተው ለጨዋታው ቀርበዋል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሃን ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ናቸው።

የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
11 አስራት ቱንጆ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
8 አማኑኤል ዮሃንስ
13 ዊሊያም ሰለሞን
15 ሬድዋን ናስር
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
14 ሀብታሙ ተከስተ
10 ሱራፌል ዳኛቸው
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም


© ሶከር ኢትዮጵያ