የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያ አሰላለፍ ታውቋል

ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን ቀድሞ ያረጋገጠው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምድቡ አንደኛ ሆኖ ማለፍን ለማረጋገጥ ከዬይ ጆይንት ስታርስ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የሚጠቀመውን አሰላለፍ ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች።

በአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኬንያ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ላይ እየተሳተፈ እንደሆነ ይታወቃል። ክለቡም ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን አድርጎ ድል በመቀዳጀት ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን ቀድሞ ያረጋገጠ ቢሆንም የምድቡ የበላይ ሆኖ ለመጨረስ የሚረዳውን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ከዬ ጆይንት ስታርስ ጋር 10 ሰዓት ላይ ያከናውናል።

በሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ከነበረው አሰላለፍ ስድስት ለውጦች የተደረጉ ሲሆን ንግስት መዓዛ፣ ታሪኳ ዴቢሶ፣ ትዕግስት ኃይሌ፣ ትዕግስት ያደታ፣ እመቤት አዲሱ፣ ፀጋነሽ ወራና ወደ አሰላለፉ መጥተው ታሪኳ በርገና፣ ትዝታ ኃይለሚካኤል፣ ብዙዓየሁ ታደሰ፣ ሰናይት ቦጋለ፣ የምስራች ላቀው፣ አረጋሽ ካልሳ አራፊ ሆነዋል።

ግብ ጠባቂ

ንግስት መዓዛ

ተከላካዮች

አለምነሽ ገረመው
ሀሳቤ ሙሶ
ትዕግስት ኃይሌ
ታሪኳ ዴቢሶ

አማካዮች

ሕይወት ደንጊሶ
ትዕግስ ያደታ
እመቤት አዲሱ

አጥቂዎች

ፀጋነሽ ወራና
መዲና ዐወል
ሎዛ አበራ