አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | አዳማ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ

ከደቂቃዎች በኋላ በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተማ ክለቦች መካከል የሚደረገውን ጨዋታ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች ይዘን ቀርበናል።

መከላከያ እና ፋሲል ከነማን በተከታታይ ረተው ለዛሬው ጨዋታ የቀረቡት አዲስ አበባ ከተማዎች ከመጨረሻው ጨዋታቸው ምንም ለውጥ ሳይደርጉ ጨዋታውን ቀርበዋል።

እስካሁን አንድ ድል ብቻ ያገኙት አዳማ ከተማዎች ደግሞ በአራተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ያለ ግብ አቻ ከተለያዩበት ፍልሚያ አራት ተጫዋቾችን ለውጠዋል። በዚህም አብዲሳ ጀማልን በአቡበከር ወንዱሙ፣ አሜ መሀመድን በፍራኦል ጫላ፣ ዮሴፍ ዮሃንስን በታደለ መንገሻ እንዲሁም ጀሚል ያዕቆብን በአሚኑ ነስሩ ተክተዋል።

12 ሰዓት ሲል የሚጀምረውን ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በዓምላክ ተሰማ የሚመራው ሲሆን ቡድኖቹም ከስር የተዘረዘሩትን ተጫዋቾች በማሰለፍ ጨዋታውን የሚጀምሩ ይሆናል።

አዳማ ከተማ

30 ጀማል ጣሰው
13 አሚኑ ነስሩ
4 ሚሊዮን ሰለሞን
80 ቶማስ ስምረቱ
8 አማኑኤል ጎበና
22 ዮናስ ገረመው
17 ታደለ መንገሻ
7 ደስታ ዮሀንስ
12 ዳዋ ሆቴሳ
27 አቡበከር ወንዱሙ
44 ፍራኦል ጫላ

 

አዲስ አበባ ከተማ

30 ዳንኤል ተሾመ
14 ልመንህ ታደሰ
6 አሰጋኸኝ ጽጥሮስ
2 ሳሙኤል አስፈሪ
18 ሙለቀን አዲሱ
20 ቻርለስ ሪባኖ
16 ያሬድ ሀሰን
9 ኤሊያስ አህመድ
7 እንዳለ ከበደ
10 ፍፁም ጥላሁን
29 ሪችሞንድ አዶንጎ