​ኢትዮጵያዊው ዳኛ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታውን ለመምራት ተሰይሟል

አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን የመራው በዓምላክ ተሰማ በአፍሪካ ዋንጫው ትልቅ ግምት የተሰጠውን ጨዋታ ለመምራት ተሰይሟል።

በካሜሩን እየተከናወነ የሚገኘውን የአፍሪካ ዋንጫ እንዲመሩ 24 ዋና 31 ረዳት እና 8 የቫር ዳኞች ከ36 ሀገራት እንደተመረጡ ይታወቃል። በእነዚህ ዝርዝሮች ውስጥ ደግሞ ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ ይገኛል። ለዚሁ ውድድር ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ስፍራው ያመራው የሀገራችን ዳኛም ዛሬ የመጀመሪያ ጨዋታውን እንደሚመራ አውቀናል።

በዚህም በምድብ አራት የሚገኙት እና በውድድሩ ትልቅ ግምት የተሰጣቸው ናይጄሪያ እና ግብፅ ከአንድ ሰዓት በኋላ የሚያደርጉትን ጨዋታ በቫር ዳኝነት ተሰይሞ እንደሚመራ ተረጋግጧል። ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞች ቀድመው ቢታወቁም ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ መለዋወጦች ቶሎ ቶሎ ስለሚመጡ እርግጠኛ መረጃ ቀድሞ ማውጣት አልተቻለም።