ኢትዮጵያ ቡና የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል

ኢትዯጵያ ቡና በሊግ ኩባንያው የተወሰነብኝ ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ቡና በመከላከያ 4-0 በሆነ ውጤት በተሸነፈበት ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የአሰልጣኝ አባላት እና የክለቡ አመራሮች ላይ አፀያፊ ስድብ ሰንዝረዋል ያለው የሊጉ አክስዮን ማኅበር የውድድር እና ሥነ ስርአት ኮሚቴ የ100 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና በ22ኛ እና በ23ኛ ሳምንት ጨዋታውን ከድሬዳዋ ከተማ እና ከወልቂጤ ከተማ ጋር ሲያደርግ ያለደጋፊዎቹ እንዲጫወት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ቡናን ውሳኔውን በመቃወም ለሊጉ አክስዮን ማህበር ተከታዩን ሀሳብ የያዘ ደብዳቤ አስገብቷል። ” ውሳኔው ክለቡን በእጅጉ የሚጎዳ እና ፍህታዊነት የጎደለው ስለሆነ ጉዳዩን በድጋሚ በማየት በቀጣይ ከድሬደዋ ከተማ እና ከወልቂጤ ከተማ ጋር በሚኖረን ጨዋታ የክለባችን ደጋፊዎቻችን ወደ ስታዲየም ገብተው እንዲደግፉ እና በተጨማሪ የአንድ መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲነሳልን በአክብሮት እንጠይቃለን።” በማለት ይግባኝ ጠይቋል።