አዲስ አዳጊዎቹ የመጀመሪያ ፈራሚያቸውን ለማግኘት ተቃርበዋል

ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደጉት ኢትዮጵያ መድኖች የመስመር ተከላካይ ለማግኘት ከጫፍ ደርሰዋል።

ከስድስት ዓመታት በኋላ ወደ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ እርከን የተመለሱት ኢትዮጵያ መድኖች ለመጪው የውድድር ዓመት ቡድናቸውን በዝውውሮች እንደሚያጠናክሩ ይጠበቃል። እስካሁን በዋና አሰልጣኝነት መንበር ላይ የሰየሙትን አሰልጣኝ ይፋ ያላደረጉት መድኖች በቀጣይ ቀናት ይህን ውሳኔያቸውን እንደሚያሳውቁ ሲጠበቅ ከዛ ቀደም ብለው ግን የዝውውር ገበያውን ለመቀላቀል በመንደርደር ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ረገድ ከከፍተኛ ሊግ አንስቶ እንዲሁም ባለፉት ሦስት የውድድር ዘመናት በሰበታ ከተማ ጥሩ ጊዜያትን ማሳለፍ የቻለው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ጌቱ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ መድን የመጀመሪያ ፈራሚ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በነገው ዕለትም ረፋድ ላይ በይፋ የክለቡ ንብረት የሚያደርገውን ፊርማ እንደሚያኖር ተሰምቷል።