ሴቶች ፕሪምየር ሊግ፡ የመካከለኛ – ሰሜን ዞን ዛሬ ሲጠናቀቅ ደደቢት 100% ሪኮርዱን አስጠብቋል

የኢትየጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ-ሰሜን ዞን የመጀመርያ ዙር ዛሬ ተጠናቋል፡፡ የ10ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታቸውን ያደረጉት ደደቢት እና ንግድ ባንክም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

በ09:00 ልደታ ክ/ከተማን የገጠመው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 7-0 በማሸነፍ አንደኛውን ዙር በሁለተኝነት አጠናቋል፡፡ ከንግድ ባንክ የድል ግቦች መካከል ሽታዬ ሲሳይ 4 ስታስቆጥር ረሂማ ዘርጋ 2 ግቦች ከመረብ አሳርፋለች፡፡ ቀሪዋን አንድ ግብ ደግም ዙለይካ ጅሃድ አስቆጥራለች፡፡

PicsArt_1460135911392

11:00 ላይ ደደቢት ከኤሌክትሪክ ባደረጉት ጨዋታ ሰማያዊ ለባሾቹ 2-0 በማሸነፍ አንደኛውን ዙር በ100% ሪኮርድ አጠናቀዋል፡፡

በጨዋታው ኤሌክትሪክ በጠንካራ መከላከል እንቅስቃሴ የጨዋታው 2/3ኛ ክፍለ ጊዜን ግብ ሳያስተናግድ ቢዘልቅም በመጨረሻም ሎዛ አበራ  ሁለት ግቦችን ከመረብ አሳርፋ ለደደቢት 3 ነጥብ አስገኝታለች፡፡

አንደኛውን ዙር ደደቢት ከ10 ጨዋታ ሙሉ 30 ነጥብ በመሰብሰብ በመሪነት ሲያጠናቅቅ ሎዛ አበራ በ10 ጨዋታዎች 26 ግቦች በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ትመራለች፡፡

 

የደረጃ ሰንጠረዥ

image

የደቡብ – ምስራቅ ዞን የአንደኛ ዙር ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል፡-

PicsArt_1460136235081

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *