የአሠልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 0-3 ኢትዮጵያ ቡና

👉”ጨዋታው ለሁለታችንም አስፈላጊ ነበር። እኛ ይበልጥ የተሻልን ነበርን ፤ የምንፈልገውን ነገርም አግኝተናል” ዮሴፍ ተስፋዬ


👉”ጨዋታው ዛሬ ጥሩ አልነበረም ፤ ቡድናችን ጥሩ አልነበረም” ይታገሱ እንዳለ

ዮሴፍ ተስፋዬ (ጊዜያዊ አሠልጣኝ) – ኢትዮጵያ ቡና

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታው ለሁለታችንም አስፈላጊ ነበር። እኛ ይበልጥ የተሻልን ነበርን ፤ የምንፈልገውን ነገርም አግኝተናል። የድካማችንን ነው ያገኘን ብዬ ነው የማስበው።

በዛሬው ጨዋታ ላይ ስላሻሻሉት ነገር….

ቡድናችን እየተሻሻለ ነው የመጣው ፤ በባለፈው ጨዋታ ብዙ ጎሎች ላይ ደርሰናል። አሁን ደግሞ የሳትናቸውን ኳሶች ወደ ግብነት ቀይረናል። ውጥረት ነው። ተጫዋቾቹ ትልቅ ቡድን ነው የገቡት። ብዙዎቹ ጫና ከሌለበት ቦታ ነው የመጡትና ያ ነገር ነው የያዛቸው እንጂ ተጫዋቾቹ ላይ አቅም ጠፍቶ አይደለም ፤ አቅም አላቸውና አሁንም በዚህ ይቀጥላሉ ብዬ ነው የማስበው።

በዕረፍት ጊዜው ለማድረግ ስላሰቡት ነገር…

በዕረፍት ጊዜ እንግዲህ ያጣነውን ነገር ፈልገን ማግኘት አለብን። የተጫዋቾቹን በራስ መተማመን መጨመር አለብን። ደካማ ጎናችን ላይ ብዙ ሠርተን እንመጣለን ብዬ አስባለሁ።

ስለ ደጋፊዎቻቸው…

እኛ ወደ ሜዳ የምንመጣው አሸንፈን ደጋፊዎቻችንን ለማስደሰት ነው። እስካሁን በነበረው ነገር በማዘናቸው በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን። ውጤት ሲጠፋ እኛም እናዝናለን ግን ሁልጊዜም ደጋፊዎቻችን መደገፍ ነው ያለባቸው። አንዳንዴ ውጤት በዚህ መልኩ ሊጠፋ ይችላል። የዛኔ ነው ይበልጥ እነሱን የምንፈልጋቸውና መደገፍ አለባቸው ነው የምለው።

ይታገሱ እንዳለ – አዳማ ከተማ

አዳማ

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታው ዛሬ ጥሩ አልነበረም ፤ ቡድናችን ጥሩ አልነበረም። አንዳንዴ ቡድን ይፈርስብሃል። ጥሩ በሆንክበት ሰዓት ጥሩ ነኝ ትላለህ እና ብዙ ከመጓጓት የተነሳ ዋጋ አስከፍሎናል።

በዕረፍት ጊዜው ለማሻሻል ስላሰቡት ነገር…

ቡድኑ ላይ የሚሻሻሉ ነገሮች አሉ። አንዳንዴ ተረጋግተን ስንመጣ የተሻለ ሜዳ ስናገኝ የተሻለ እንቅስቃሴ እናደርጋለን ብዬ አስባለሁ።