ዋሊድ በቋሚነት በተሰለፈበት ጨዋታ ኦስተርሰንድስ በሜዳው ተሸንፏል 

በስዊድን ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ኦስተርሰንድስ በሜዳው እና ደጋፊው ፊት በኤአይኬ 2-0 ተሸንፏል፡፡ የኦስተርሰንድስን የተከላካይ መስመር ከወዲሁ መምራት የጀመረው ዋሊድ ሙሉ 90 ደቂቃ ተሰልፎ መጨዋት የቻለ ሲሆን የቀድሞ ክለቡን ኤአይኬን ተቃራኒ ሆኖ ገጥሟል፡፡

ለኤአይኬ የድል ግቦቹን ካርሎስ ስትራድበርግ እና አሌክስ አንደር አይዛክ በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡ አዲስ መጪው ኦስተርሰንድስ በሊጉ መክፈቻ ጨዋታ አቻ ሲለያይ እስካሁን ማሸነፍ አልቻለም፡፡ ሽንፈቱን ተከትሎ ኦስተርሰንድስ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ በ1 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *