የካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች አርብ ሲጀመሩ የዩጋንዳው ቪላ በኤፍዩኤስ ራባት የጎል ናዳ ወርዶበታል፡፡ የአልጄሪያው ኮንስታንታይን የግብፁን ምስር ኤል ማቃሳን በባከነ ደቂቃ 1-0 ሲያሸንፍ ኤምሲ ኦራን ከካውካብ ማራካሽ እንዲሁም ዛናኮ ከስታደ ጋቢሲየን አቻ ተለያይተዋል፡፡
ኤፍዩኤስ ራባት አርብ ምሽት በሞሮኮ ዋና ከተማ በተካሄደ ጨዋታ ቪላን 7-0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ከጫፍ ደርሷል፡፡ በዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዩሪ ሞሴቪኒ የገንዘብ ድጋፍ ወደ ሞሮኮ ያቀኑት ቪላዎች ከወዲሁ የማለፍ ተስፋቸውን ያጨለመ ውጤትን ይዘው ወደ ካምፖላ ተመልሰዋል፡፡ ለ2010 የኮንፌድሬሽን ካፕ አሸናፊው ሰባቱን ግቦች ሞራድ ባትና፣ መሃም ፋውዚር፣ ሲ ማንዳው፣ አብዱልሰላም ቤንጆለም፣ ኤል መህዲ ኤል ባሲል፣ ማርዋን ሳዳል እና የሱፍ ኤል ጉናዊ አስቆጥረዋል፡፡
ሲኤስ ኮንታንታይን ምስር ኤል ማቃሳን 1-0 አሸንፏል፡፡ የኮንታንታይንን የድል ግብ መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ በተጨመሩ የባከኑ ደቂቃዎች ውስጥ የቀድሞው የላዝዮ ኮከብ ሙራድ መግኒ በቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡
ኤምሲ አራን እና ከካውካብ ማራካሽ ጨዋታቸውን ካለግብ አቻ በመለያየት አጠናቅቀዋል፡፡ ወደ ሉሳካ ያቀናው የቱኒዚያው ስታደ ጋቢሲየን ከዜናኮ ጋር 1-1 ተለያይቷል፡፡

የአርብ ውጤት
ፋስ ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ) 7-0 ስፖርት ክለብ ቪላ (ዩጋንዳ)
የቅዳሜ ውጤቶች
መውሊዲያ ክለብ ደ ኦራን (አልጄሪያ) 0-0 ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ)
ሲኤስ ኮንስታንታይን (አልጄሪያ) 1-0 ምስር ኤል ማቃሳ (ግብፅ)
ዜናኮ (ዛምቢያ) 1-1 ስታደ ጋቢሲየን (ቱኒዚያ)