ሲዳማ ቡና 1-2 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
49′ ሳውሬል ኦልሪሽ
29′ ጋብሬል አህመድ, 40′ ቢንያም በላይ
ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከሶከር ኢትዮጵያ
ተጠናቀቀ
ጨዋታው በንግድ ባንክ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ሀምራዊ ለባሾቹም ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፈዋል፡፡
የተጫዋች ለውጥ
89′ ቢንያም በላይ ወጥቶ ቢንያም አሰፋ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
83′ ፍቅረየሱስ ወጥቶ አብዱልከሪም ሀሰን ገብቷል፡፡
ቀይ ካርድ
78′ ፊሊፕ ዳውዚ ሳይነካ ወድቋል በሚል በ2ኛ ቢጫ ከሜዳ ተወግዷል፡፡
75′ ክፍሌ በባንክ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ቢወድቅም አርቢቴር አማኑኤል በዝምታ አልፈውታል፡፡ የሲዳማ ተጫዋቾችም የፍጹም ቅጣት ምት ይገባናል ብለው ተቃውመዋል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
66′ ሰለሞን ገብረመድህን ወጥቶ ሲሳይ ቶሊ ገብቷል
60′ ጨዋታው እንደ መጀመርያው አጋማሽ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡
49′ ጎልልል!!!! ሲዳማ ቡና
ሳውሬል ኦልሪሽ ከቅጣት ምት ግብ አስቆጥሮ ሲዳማን ወደ ጨዋታው መልሶታል፡፡
ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡
የእረፍት ሰአት ቅያሪ
ፋሲል ባቱ ወጥቶ ክፍሌ ኪአ ገብቷል፡፡
– – – – –
እረፍት
የመጀመሪያው አጋማሽ በባንክ 2-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡
* ጨዋታው ቀዝቃዛ እነንቅስቃሴ እየተደረገበት ይገኛል፡፡
40′ ጎልልል!!! ንግድ ባንክ
ቢንያም በላይ ከተከላካዮች አምልጠ ጦበመውጣት የባንክን 2ኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
29′ ጎልልል!!!! – ንግድ ባንክ
ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ጋብሬል በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሯል፡፡
ቢጫ ካርድ
28′ ፊሊፕ ዳውዚ ኦልሪሽ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
26′ ፊሊፕ ዳውዚ የሞከረው ኳስ በተከላካዮች ሲመለስ ፍቅረየሱስ አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
20′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እደተደረገበት ይገኛል፡፡ ይህ ነው የሚባል የግብ ሙከራም አልተደረገም
ተጀመረ
1′ ጨዋታው ተጀምሯል፡፡ ሲዳማ ከቀኝ ወደ ግራ ፣ ባንክ ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃሉ፡፡
የሲዳማ ቡና አሰላለፍ
አዱኛ ጸጋዬ
ዘነበ ከበደ – አንተነህ ተስፋዬ – ተመስገን ካስትሮ – ሳውሬል ኦልሪሽ
አዲስ ግደይ – ሙሉአለም መስፍን – ፍፁም ተፈሪ – ፋሲል ባቱ – ወሰኑ ማዜ
ላኪ በሪለዱም ሰኒ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ
ኢማኑኤል ፌቨር
ዳንኤል አድሃኖም – ቢንያም ሲራጅ – ቶክ ጀምስ – አንተነህ ገብረክርስቶስ
ጋብሬል አህመድ – ሰለሞን ገብረመድህን
ኤፍሬም አሻሞ – ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን – ቢንያም በላይ
ፊሊፕ ዳውዚ