ሊግ ዋንጫ: ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ቡና 0-0 (2-4) አዳማ ከተማ

ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከሶከር ኢትዮጵያ

ተጠናቀቀ!!!!
ጨዋታው በአዳማ 4-2 አሸናፊነት (መለያ ምት) ተጠናቋል፡፡

4ኛ ምት (አዳማ) ፋሲካ አስፋው አገባ 2-4
4ኛ ምት (ቡና) ወንድይራው ጌታሁን ሳተ 2-3
3ኛ ምት (አዳማ) ፡ እሸቱ መና አገባ 2-3
3ኛ ምት (ቡና) ፡ አክሊሉ ዋለልኝ አገባ 2-2
2ኛ ምት (አዳማ) ፡ ሞገስ ታደሰ አገባ 1-2
2ኛ ምት (ቡና) ፡ ኤልያስ ማሞ አገባ 1-1
1ኛ ምት (አዳማ) ፡ ወንድሜነህ ዘሪሁን አገባ 0-1
1ኛ ምት (ቡና) : ያቤውን ዊልያም ሳተ 0-0

ሁለቱ ቡድኖች ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡ በግራ በኩል (ዳፍ ትራክ አቅጣጫ) ባለው ጎል ላይ ይመታሉ፡፡
– – – – – –
ተጠናቀቀ
ጨዋታው ካለግብ ተጠናቋል፡፡ አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት የሚያመሩ ይሆናል፡፡

90′ መደበኛው ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

88′ ንዳዬ ፋይስ ጥሩ የማግባት አጋጣሚ ቢያገኝም ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
83′
ጫላ ድሪባ ወጥቶ ቢንያም አየለ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ አዳማ
81′
ዮናታን ከበደ ወጥቶ ወንድሜነህ ዘሪሁን ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
80′
ጋቶች ፓኖም ወጥቶ አክሊሉ ዋለልኝ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
70′
እያሱ ታምሩ ወጥቶ አማኑኤል ዮሃንስ ገብቷል

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
62′
ጥላሁን ወልዴ ወጥቶ ንዳዬ ፋይስ ገብቷል፡፡

59′ ተስፋዬ ነጋሽ ከርቀት የመታው ኳስ በግቡ ቋሚ በኩል ለጥቂት ወጥቷል፡፡

58′ ኤልያስ ማሞ ከቅጣት ምት የሞከረው ኳስ የግቡ ቋሚ መልሶበታል፡፡

56′ ጫላ ድሪባ ከሀሪሰን ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የሞከረውን ኳስ ሀሪሰን አድኖታል፡፡

ቢጫ ካርድ
54′
ጫላ ድሪባ በጋቶች ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

50′ ኤፍሬም ወንድወሰን የሞከረውን ኳስ ሞገስ እና ጃኮብ ተረባርበው አውጥተውታል፡፡

ቢጫ ካርድ
47′
ኤልያስ ማሞ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

46′ ዮናታን ከበደ የፍጹም ቅጣት ምቱን ስቶታል፡፡

ፍፁም ቅጣት ምት
46′
ተስፋዬ ላይ በተሰራው ጥፋት አዳማ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቷል፡፡

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀመረ

– – – – – –
 
እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ ካለግብ ተጠናቋል፡፡

40′ ደቂቃው ልክ 40 ሲደርስ የቡና ደጋፊዎች በአመራር ላይ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በ20ኛው ደቂቃም በተመሳሳይ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

39′ ኤልያስ ማሞ ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡

38′ ኤልያስ ማሞ በጥሩ ሁኔታ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ገብቶ የሞከረውን ኳስ ተከላካዮች ተደርበው አውጥተውታል፡፡

30′ ኢትዮጵያ ቡና ጫና ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም እስካሁን ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ አልቻለም፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
26′ ተስፋዬ በቀለ በጉዳት ወጥቶ እሸቱ መና ገብቷል፡፡ ‘ጃምቦ’ ከቀድሞ ክለቡ ቡና ደጋፊዎች ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተለግሶታል፡፡

24′ ታከለ አለማየው በመልሶ ማጥቃት የመጣውን ኳስ ከርቀት ሞክሮ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

19′ ያቤውን ዊልያም ከርቀት የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

10′ ጨዋታው በመሀል ሜዳ ላይ ያመዘነ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በቡና አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

* የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የጀመረ ተቃውሞ በቡና አመራሮች በተለይም በስራ አስኪያጁ ገዛኸኝ ወልዴ ላይ እያሰሙ ይገኛሉ፡፡ በስፔን የተቃውሞ ምልክት የሆነውን ነጭ ጨርቅ ማውለብለብም የተቃውሞው አካል ነው፡፡
– – – – –
የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ

ሀሪሰን ሀሶው

አብዱልከሪም መሀመድ – ወንድይፍራው ጌታሁን ኤፍሬም ወንድወሰን- ሳለአምላክ ተገኝ

ጋቶች ፓኖም – መስኡድ መሃመድ – ኤልያስ ማሞ

ጥላሁን ወልዴ – ያቤውን ዊልያም – እያሱ ታምሩ

 

የአዳማ ከተማ አሰላለፍ

ጃኮብ ፔንዛ

ምንተስኖት አበራ – ተስፋዬ በቀለ – ሞገስ ታደሰ – ሱሌማን መሃመድ

ታከለ አለማየሁ – ብሩክ ቃለቦሬ – ፋሲካ አስፋው – ዮናታን ከበደ

ተስፋዬ ነጋሽ – ጫላ ድሪባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *