የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የአዲስ አበባ ሴቶች ከፍተኛ ዲቪዝዮን የ4 ሳምንታት ውድድሮችን አድርጓል፡፡ የካቲት 17 ቀን 2008 የተጀመረው የዘንድሮው የውድድር ዘመን የሁለት ሳምንተ ጨዋታ ካደረገ በኋላ በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ምክንያት ተቋርጦ ቆይቶ መጋቢት 27 ካቆመበት ቀጥሏል፡፡
ቅዳሜ በተደረጉ የ4ኛ ሳምንት ጨዋታዎች 3፡00 ላይ ቂርቆስ ብሩህ ተስፋን 5-1 ሲረታ 5፡00 ላይ አቃቂ አሜንን 5-0 አሸንፏል፡፡ 07፡00 ሊደረግ የነበረው የቦሌ እና ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ጨዋታ የቦሌ ቡድን መሪ ባለመገኘቱ ምክንያት ለአካዳሚ ፎርፌ (3 ነጥብ እና 3 ጎል) ሲሰጥ ለቦሌ 0 ጎል እና 0 ነጥብ ተመዝግቧል፡፡ ትላንት 3፡00 ላይ በተደረገ አንድ ጨዋታ ደግሞ ጉለሌ ከ አስኮ 1-1 ተለያይተዋል፡፡
የደረጀ ሰንጠረዥ
ተጨማሪ መረጃዎች – ትዕንግርት እግርኳስ ክለብ