የሱፍ ሳላ አሁንም አዲስ ክለብ እየፈለገ ነው 

ኢትዮጵያዊው የመስመር አማካይ የሱፍ ሳላ $በጥር ወር መጀመሪያ የስዊድን ሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለብ የሆነውን ኤኤፍሲ ዩናይትድን ከለቀቀ በኃላ ለሌላ አዲስ ክለብ አስካሁን መፈረም አልቻለም፡፡

የሱፍ በጥር ወር መጀመሪያ ለዕረፍት አዲስ አበባ በመጣበት ወቅት ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት የተሻለ ውል ለሚያቀርብለት ክለብ ለመጫወት እንደሚወስን መናገሩ ይታወሳል፡፡ ተጫዋቹ በኤኤፍሲ ዩናይትድ በነበረው የአጭር ግዜ ውልን አጠናቅቆ በዓመቱ መጀመሪያ አዲስ ክለብን ይቀላቀላል ተብሎ ቢጠብቅም እስካሁን ወደ ሌላ ክለብ አለማምራቱን የሱፍ ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጧል፡፡

የሱፍ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደ ሌላ የማምራቱ ጉዳይ እንዳማይቀር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ባርሰሎና ስፔን የሚገኘው የ31 ዓመቱ የሱፍ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት ከወኪሉ ጋር ለአዲስ ክለብ ለመፈረም እየተደራደረ ይገኛል፡፡ “እኔ አሁን ባርሰሎና ነው ያለሁት፡፡ ስለቀጣይ ክለቤ ከወኪሌ ጋር በመወያየት ላይ እገኛለው፡፡ ወኪሌ አዲስ ክለብ እንዳገኘልኝ ገና እያየሁ ስለሆን እስካሁን ወደ ሌላ ክለብ አልተዛወርኩም፡፡” ሲል ሃሳቡን አጠናቅቋል፡፡

የሱፍ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብድን ለ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ከተሰለፈ በኃላ ለዋልያዎቹ እልተጠራም፡፡ በኤኤፍሲ ዩናይትድም ለተወሰኑ ወራት በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ተገልሎ ነበር፡፡ የሱፍ አሁን በመልካም ጤንነት ላይ ሲገኝ ጠንካራ ልምምድም በግሉ እየሰራ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *