ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 መከላከያ
13′ በሃይሉ አሰፋ
73′ ምንተስኖት አዳነ
– – – – – – – –
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ፈረሰኞቹም የሊጉን መሪነት ከተከታዩ ደደቢት በ4 ነጥብ ርቀው አንደኛውን ዙር አጠናቀዋል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 5 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

87′ ሳሙኤል ሳሊሶ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
86′
አዳነ ግርማ ወጥቶ ዳዋ ሁቴሳ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
77′
ሚካኤል ደስታ ወጥቶ ሳሙኤል ሳሊሶ ገብቷል፡፡

76′ አዳነ ግርማ ከርቀት የመታው ኳስ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ሲመለስ በሃይሉ አሰፋ ሞክሮ ጀማል አውጥቶበታል፡፡

ቢጫ ካርድ – መከላከያ
75′
በሃይሉ ግርማ ናትናኤል ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
73′ ምንተስኖት አዳነ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ አስቆጥሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
70′
ምንያህል ተሾመ ወጥቶ ናትናኤል ዘለቀ ገብቷል፡፡

67′ ራምኬል ሎክ ከመከላከያ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ጠርዝ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

65′ ማራኪ ወርቁ ከቀኝ መስመር የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደ ላይ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
61′
ነጂብ ሳኒ በሃይሉ አሰፋ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
59′
በሃይሉ አሰፋ ፍሬው ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

58′ በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ወጥ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻሉም፡፡ ቅብብሎች ቶሎ ቶሎ ሲቋረጡ የግብ ሙከራዎችም አልታዩም፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
54′
ካርሎስ ዳምጠው ወጥቶ ማራኪ ወርቁ ገብቷል፡፡

ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ

– – – –
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45+2′ አበባው ቡታቆ የመታውን ቅጣት ምት ጀማል አውጥቶበታል፡፡

45+1′ አሉላ ግርማ (ጉዳት) ወጥቶ አንዳርጋቸው ይላቅ ገብቷል፡፡ አሉላ ጉልበቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ከሜዳ የወጣው በተጫዋቾች ድጋፍ ሲሆን ቃሬዛ አለመዘጋጀቱ ተመልካቹን አስቆጥቷል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

34′ ባዬ ከፍሬው የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ የሞከረውን ኳስ ኦዶንካራ ሲመልስበት ባዬ በድጋሚ አግኝቶ ሲሞክረው አስቻለው ተደርቦ አውጥቶታል፡፡

30′ በሃይሉ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ቀኝ መስመር የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

29′ ባዬ ገዛኸኝ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ሮበርት ኦዶንካራ ይዞበታል፡፡

25′ በግራ ጥላ ፎቅ የሚገኙ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ፌዴሬሽኑ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ያወጣውን ህግ እንዲያከብር በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

22′ ካርሎስ ዳምጠው ከባዬ የተሻገረለትን ኳስ አየር ላይ ተንሳፎ ቢመታውም ኦዶንካራ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

13′ ጎልልል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
በሃይሉ አሰፋ የግብ ጠባቂውን መውጣት ተመልክቶ የመታው ኳስ መረብ ላይ አርፏል፡፡

12′ ባዬ ገዛኸኝ ከግቡ የግራ መስመር የቅርብ ርቀት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

2′ ተስፋዬ አለባቸው ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ
1′
ጨዋታው በጊዮርጊስ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡ ጊዮርጊስ ከቀኝ ወደ ግራ መከላከያ ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃሉ፡፡

*ልክ የዛሬ አመት በዛሬው ቀን የመከላከያ ተጫዋች የነበረው ተክለወልድ ፍቃዱ በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፡፡ ተጫዋቹ ህይወቱ ከማለፉ በፊት የመጨረሻ ጨዋታውን ያደረገው መከላከያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ነበር፡፡

ማልያ
ቅዱስ ጊዮርጊስ
: ቀይ – ቢጫ – ቢጫ
መከላከያ : አረንጓዴ/ቀይ – አረንጓዴ – ቀይ

11:05 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው በማሟሟቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
– – – – –

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ (4-3-3)
30 ሮበርት ኦዶንካራ
6 አሉላ ግርማ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 15 አስቻለው ታመነ – 4 አበባው ቡታቆ
9 ምንያህል ተሾመ – 21 ተስፋዬ አለባቸው – 23 ምንተስኖት አዳነ
18 ራምኬል ሎክ – 19 አዳነ ግርማ – 7 በኃይሉ አሰፋ

ተጠባባቂዎች
1 ፍሬው ጌታሁን
5 አይዛክ ኢዜንዴ
20 ዘካርያስ ቱጂ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ
17 አቡበከር ሳኒ
11 ዳዋ ሁቴሳ
26 ናትናኤል ዘለቀ

የመከላከያ አሰላለፍ (4-4-2)
1 ጀማል ጣሰው
25 ታፈሰ ሰርካ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ – 4 ነጂብ ሳኒ
13 ሚካኤል ደስታ (አምበል) – 21በሃይሉ ግርማ – 10ፍሬው ሰለሞን – 19 ሳሙኤል ታዬ
11 ካርሎስ ዳምጠው – 12 ባዬ ገዛኸኝ

ተጠባባቂዎች
22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
20 ሚልዮን በየነ
29 ሙሉቀን ደሳለኝ
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
7 ማራኪ ወርቁ
26 ኡጉታ ኦዶክ
9 ሳሙኤል ሳሊሶ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *