ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ከሰኔ 9-12 ይካሄዳል

በኢትየጵያ የሚገኙ የስፖርት ክለቦች ፣ የስፖርት ቁሳቁስ አምራች እና አከፋፋዮች እና ከስፖርት ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት 2ኛው ሃገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚብሽን እና ባዛር ከሰኔ 9-12 እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ጂኤምኤስ ፣ ፈለቀ ደምሴ ማስታወቂያ እና ፕሬስ እንዲሁም የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቀዋል፡፡

ዛሬ ረፋድ በብሄራዊ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከጂኤምኤስ አቶ ዘላለም ፍስሃ ከፈለቀ ደምሴ የማስታወቂያ ድርጅት ጋዜጠኛ ፈለቀ ደምሴ እንዲሁም ከወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር አቶ መኮንን የተገኙ ሲሆን የባዛሩ አላማ በስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ምርት እና አገልግሎት የሚያስተዋውቁበትን ፣ አዳደስ ደጋፊ የሚፈጥሩበት ፣ እርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠነክሩበትን ፣ የስፖርት ኢንቨስትመንት ግንዛቤ የሚፍጠርበትን ፣ ክለቦች ከቁሳቁስ ሽያጭ ገቢ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በዘንድሮው ኤግዝብሽን እና ባዛር ላይ እንደሚካፈሉ ማረጋገጫ የሰጡት አካላት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፣ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ዳሽን ቢራ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ኢትዮጵያ ቡና  እና ደደቢት መሆናቸው ሲገለፅ አምና ከተሳተፉት አካላት መካከል 90 በመቶው ዘንድሮም ይካፈላሉ ተብሏል፡፡

በባዛሩ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ አካላት ለመመዝገቢያ እንደየደረጃው ከ5ሺህ – 20ሺህ ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *