የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ለመልሱ ጨዋታ በአዳማ የሚያደርገውን ዝግጅት ቀጥሏል

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከሶማልያ ለሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ በአዳማ ከተማ  የሚያደርጉትን ዝግጅት ቀጥለዋል፡፡

ቡድኑ በመጀመርያ አዳማ ጀርመን ሆቴል ከትሞ የነበረ ሲሆን በምግብ አለመመቸት ምክንያት ከሁለት ቀን ቆይታ በኋላ አዳማ ራስ ሆቴል አዙረዋል፡፡

ቡድኑ 25 ተጨዋቾችን በመያዝ ቅዳሜ አዳማ የገቡ ሲሆን ሰኞ ቢኒያም ተቀላቅሎ በአጠቃላይ 26 ተጨዋቾች ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከሰኞ እስከ ረቡዕም በቀን ሁለቴ ልምምዳቸውን ሰርተዋል፡፡

ቡድኑ በዛሬው እለት አዳማ ከሚገኘው የሙገር ተስፋ ቡድን ጋር የዝግጅት ጨዋታ ያደረጉ ሲሆን ትላንት በልምምድ ላይ መጠነኛ ጉዳት ያጋጠማቸው ቢኒያም በላይ እና ኦሜ መሀመድ በዛሬው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ አልተሰለፉም፡፡

በቀሪው ቀናት የወዳጅነት ጨዋታ የዝግጅቱ አካል ሲሆን እሁድ ወይም ሰኞ ከአዳማ የተስፋ ቡድን ጋር ጨዋታ አድርገው ሰኞ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ አንድ ቀን እረፍት አድርገው ረቡዕ ወደ ጅቡቲ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከሶማልያ ከ20 አመት ብሄራዊ ጋር የሚደረገው የመልስ ጨዋታ አርብ 21/08/08 በጅቡቲ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *