የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የአዲስ አበባ ተስፋ ቡድኖች ውድድር የሁለተኛ ዙር ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡
በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ምክንያት 10ኛው ሳምንት ላይ ተቋርጦ የነበረው ይህ ውድድር መጋቢት 24 እና 25 ቀጥሎ የመጀመርያው ዙር የመጨረሻ ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ መከላከያ ሰውነት ቢሻውን በፎርፌ ሲረታ ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ቅዱስ ጊዮርጊስን ፣ ንግድ ባንክ መድንን በተመሳሳይ 1-0 ፣ ኤሌክትሪክ ሙገርን 3-1 ፣ አዳማ ከተማ ደደቢትን 2-0 አሸንፈዋል፡፡
የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ቅዳሜ ሚያዝያ 8 ቀን 2008
03፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኤሌክትሪክ
05፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ መድን
08፡00 ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከ ኢትዮጵያ ቡና
10፡00 ደደቢት ከ መከላከያ
እሁድ ሚያዝያ 9 ቀን 2008
5፡00 አዳማ ከተማ ከ ሙገር ሲሚንቶ
-ሰውነት ቢሻው በዚህ ሳምንት አራፊ ነው
የደረጃ ሰንጠረዥ