የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ዙር ነገ ይጀመራል፡፡ በቡድኖቹ የ1ኛ ዙር ጠንካራ እና ደካማ ጎን እንዲሁም ለውጦችን በ2 ክፍሎች የዳሰሰችው ሶከር ኢትዮጵያ በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ እና ከወገብ በታች ያሉትን 7 ክለቦች በክፍል ሶስት አጠር አድርገን አቅርበነዋል፡፡
መከላከያ
ደረጃ – 8ኛ
ተጫወተ – 13 ፣ አሸነፈ – 4 ፣ አቻ – 4 ፣ ተሸነፈ – 5 ፣ አገባ – 11 ፣ ገባበት – 10
የዲሲፕሊን ሪኮርድ – ቢጫ ካርድ 18 ፣ ቀይ ካርድ – 0
ጠንካራ ጎን ፡ ኳስ ይቆጣጠራሉ ፣ የተከላካይ መስመሩ በንጽጽር ጠንካራ ነው፡፡
ደካማ ጎን ፡ ግብ የማስቆጠር እና የግብ እድል የመፍጠር ችግር ይታይባቸዋል
ለውጦች – አዲስ የገባ ተጫዋችም ሆነ የለቀቀ ተጫዋች የለም፡፡
ኤሌክትሪክ
ደረጃ – 9ኛ
ተጫወተ – 13 ፣ አሸነፈ – 4 ፣ አቻ – 4 ፣ ተሸነፈ – 5 ፣ አገባ – 12 ፣ ገባበት – 13
የዲሲፕሊን ሪኮርድ ፡ ቢጫ ካርድ ቀይ ካርድ 31 ፣ ቀይ ካርድ – 2
ጠንካራ ጎን ፡ የተከላካይ መስመሩ ከሌሎች ክፍሎች በአንጻራዊነት የተሸለ ነው፡፡ አጥቂዎቹ ከሚያገኟቸው የግብ እድሎች አንጻር የግ ማስቆጠር አቅማቸው ከፍ ያለ ነው፡፡
ደካማ ጎን ፡ እንደቡድን የተደራጀ እንቅስቃሴ አያደርጉም ፣ ቡድኑ በየጨዋታ ክፍሎች ያለው መናበብ ደካማ ነው፡፡ በተለይም የአማካይ ክፍሉ የማጥቃት ፣ የመከላከል እና የቦታ አያያዝ ችግሮች ታይባቸዋል፡፡
ለውጦች – አዲስ የገባም ሆነ የወጣ ተጫዋች የለም
ሀዋሳ ከተማ
ደረጃ – 10ኛ
ተጫወተ – 13 ፣ አሸነፈ – 4 ፣ አቻ – 4 ፣ ተሸነፈ – 5 ፣ አገባ – 14 ፣ ገባበት – 18
የዲሲፕሊን ሪኮርድ – ቢጫ ካርድ – 16 ፣ ቀይ ካርድ – 1
ጠንካራ ጎን – ኳስ ቁጥጥር ላይ ጥሩ ናቸው፡፡
ደካማ ጎን – ያጥቃት እቅስቃሴያቸው ደካማ ሲሆን ብዙ የግብ እድሎችንም አይፈጥሩም፡፡
ለውጦች ፡ መዳህኔ ታደሰ ድሬዳዋ ከተማ ለመፈረም ተስማምቶ በመጨረሻም ሀሳቡን በመቀየር ወደ ሀዋሳ አምርቷል፡፡ መስቀሌ መንግስቱ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና ሲያመራ መክብብ ደገፉ ወደ ወላይታ ድቻ አቅንቷል፡፡ አመለ ሚልኪያስ እና ገብረሚካኤል ያዕቆብ ወደ ቀድሞ ክለባቸው አርባምንጭ አምርተዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ በጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ተመስገን ተክሌ ማገገም ለሀዋሳ መልካም ዜና ነው፡፡
ኢትዮጵያ ቡና
ደረጃ – 11ኛ
ተጫወተ – 13 ፣ አሸነፈ – 4 ፣ አቻ – 3 ፣ ተሸነፈ – 6 ፣ አገባ – 12 ፣ ገባበት – 14
የዲሲፕሊን ሪኮርድ – ቢጫ ካርድ – 16 ፣ ቀይ ካርድ – 0
ጠንካራ ጎን – ከሌሎች ቡድኖች በንፅፅር በከፍተኛ ፍጥነት ይጫወታሉ፡፡ የአሰልጣኙ አጨዋወት ጥራት ባላቸው ተጫዋቾች ቢሆን ምናልባት የተሻለ የውድድር ዘመን ያሳልፉ ነበር፡፡
ደካማ ጎን – ወጥ አቋም ማሳየት ይቸገራል ፣ እንደቀደሙት አመታት ሁሉ ዘንድሮም በክልል ጨዋታዎች ላይ ድል ማሳካት ተስኗቸዋል፡፡
ለውጦች ፡ ንዳዬ ፋይስ ፣ ፓትሪክ ቤናውን እና ኤርሚያስ በለጠ ቀደም ብለው ፈርመው በሊጉ ጨዋታዎች ላይ በመሰለፋቸው ውዝግቦች የተከተሉ ሲሆን ተጨማሪ ተጫዋቾች ቡናን አልተቀላቀሉም፡፡ ቀፃ ፍቅረማርያም እና ሀብታሙ ደግሞ በውሰት ወደ ኢትዮጵያ መድን አምርተዋል፡፡
አርባምንጭ ከተማ
ደረጃ – 12ኛ
ተጫወተ 13 ፣ አሸነፈ 3 ፣ አቻ 5 ፣ ተሸነፈ 5 ፣ አገባ 10 ፣ ገባበት 12
የዲሲፕሊን ሪኮርድ ፡ ቢጫ ካርድ 23 ፣ ቀይ ካርድ 1
ጠንካራ ጎን – የተከላካይ መስመሩ በንፅፅር የተሻለ ነው፡፡ ቡድኑ የሚገኝበት ደረጃ እና የተቆጠረበትን ግብ ከግምት ስናስገባ የተሻለ የመከላከል አጨዋወት እንዳለው እንረዳለን፡፡
ደካማ ጎን – ግብ ማስቆጠር የቡድኑ ዋንኛ ችግር ነው፡፡ አዳዲስ ተጫዋቾች ቡድኑን መቀላቀላቸው ምናልባት ይህንን ችር ሊቀርፈው ይችላል፡፡
ለውጦች ፡ ገብረሚካኤል ያዕቆብ እና አመለ ሚልኪያስ ከሀዋሳ ከተማ ፣ እንዳለ ከበደ ከሲዳማ ቡና እንዲሁም ቢያድግልኝ ኤልያስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቀድሞ ክለባቸው የተመለሱ ሲሆን ምንም ተጫዋች ከቡድኑ አለቀቀም፡፡
ዳሽን ቢራ
ደረጃ – 13ኛ
ተጫወተ 13 ፣ አሸነፈ 3 ፣ አቻ 4 ፣ ተሸነፈ 6 ፣ አገባ – 6 ፣ ገባበት 10
የዲሲፕሊን ሪኮርድ ፡ ቢጫ ካርድ 27 ፣ ቀይ ካርድ 0
ጠንካራ ጎን – የተከላካይ መስመሩ ዘንድሮም ጠንካራ ነው፡፡
ደካማ ጎን – ይህ ነው የሚባል የጨዋታ ስትራቴጂ የለውም፡፡ በጨዋታ የሚፈጥሩት የግብ እድል እጅግ በጣም ጥቂት ነው፡፡ በሊጉ ትንሽ ግብ ያስቆጠረው ቡድንም ዳሽን ቢራ ነው፡፡
ለውጦች ፡ አዲስ ተጫዋች ያልፈረመ ሲሆን ያሬድ ዘውድነህ እና መድሃኔ ታደሰ ክለቡን ለቀዋል፡፡
ሀዲያ ሆሳዕና
ደረጃ – 14ኛ
ተጫወተ 13 ፣ አሸነፈ 1 ፣ አቻ 2 ፣ ተሸነፈ 10 አገባ 13 ፣ ገባበት 22
የዲሲፕሊን ሪኮርድ – ቢጫ ካርድ 18 ፣ ቀይ ካርድ 2
ጠንካራ ጎን ፡ በጥቂት ተጫዋቾች ላይ የተንጠለጠለ ቢሆንም ግብ የማስቆጠር ብቃታቸው እና የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴያቸው መልካም ነው፡፡
ደካማ ጎን ፡ ቡድኑ ከብሄራዊ ሊጉ ከባቢ አልወጣም፡፡ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በአጋጣሚ እንደመጣ የሜዳ እንቅስቃሴያቸው ላይ ይነበባል፡፡ የሊግ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ጥቂት መሆን የቡድኑን ደረጃ አውርዶታል፡፡
ለውጦች ፡ ቢንያም ታዬ ፣ አትክልት ስብሃት ፣ መስቀሌ መንግስቱ ፣ ወንድማገኝ ተሾመ ፣ ሀይደር ሸረፋ ፣ አልፋየሁ ሙላቱ ፣ ተመስገን ገብረጻዲቅ ፣ አሸናፊ አደም እና ሙሴ ገብረኪዳን ሲቀላቀሉ ካሳሁን ገረመው ፣ አበባየሁ ዮሃንስ እና ሀብቴ ከድርን ጨምሮ 5 ተጫዋቾች ለቀዋል፡፡