ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-1 አዳማ ከተማ
39′ ራምኬል ሎክ | 37′ ጫላ ድሪባ
—————-
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡ ግብ ጠባቂው ጃኮብ ከዳኛው ጋር በፈጠረው ውዝግብ የቀይ ካርድ ሰለባ ሆኗል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
84′ ጫላ ድሪባ ወጥቶ ሻኪሩ አላዴ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
81′ ራምኬል ሎክ ወጥቶ ጎድዊን ቺካ ገብቷል፡፡
80′ ፋሲካ አስፋው ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
79′ አስቻለው ታመነ እና ጫላ ድሪባ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል፡፡
ቢጫ ካርድ
77′ እሸቱ መና በበሃይሉ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
75′ ምንያህል ተሾመ ወጥቶ ናትናኤል ዘለቀ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
74′ ታፈሰ ተስፋዬ ወጥቶ ተስፋዬ ነጋሽ ገብቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
67′ ጃኮብ ኳስ አላግባብ በማዘግየቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ በውሳኔው ከአርቢቴር ይርጋለም ጋር እሰጣገባ ውስጥ የገባው ታፈሰ ተስፋዬም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
60′ ወንድሜነህ ዘሪሁን የሞከረው ኳስ በተከላካዮች ተጨርፎ ወጥቷል፡፡ ከ1 ደቂቃ በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ ሙከራ አድርጎ የግቡን ቋሚ ታኮ ወጥቶበታል፡፡
57′ በሃይሉ አሰፋ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ሳላዲን ሰኢድ በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት ወጥቶበታል፡፡
55′ ሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመርያው ፍፁም በተለየ መልኩ የተቀዛቀዘ ሆኗል፡፡
ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ከ40 ደቂቃ ‘እረፍት’ በኋላ ተጀመረ
የእረፍት ሰአት ለውጥ
ተስፋዬ አለባቸው ወጥቶ ሳላዲን ሰኢድ ገብቷል፡፡
————
* ጨዋታው እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡
* ኮሚሽነሩ እና ዳኞች ጨዋታውን በመቀጠል እና በማቋረጥ ላይ እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡
* ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ ወጥተዋል፡፡ የጨዋታው ኮሚሽነር ተጨማሪ ሃይል እንዲመጣ እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡
*** 2ኛው አጋማሽ እስካሁን አልተጀመረም፡፡
*** በርካታ ደጋፊዎች በውርወራው ጉዳት ደርሶባቸው የመጀመርያ ደረጃ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
*** በሚስማር ተራ እና ቀኝ ካታንጋ አካባቢ በአዳማ እና ጊዮርጊስ ደጋፊዎች መካከል የድንጋይ ውርወራን ጨምሮ ከፍተኛ ግርግር ፈጥረዋል፡፡ ከመጀመርያው አጋማሽ የመጨረሻ ደቂቃ የጀመረው ግርግር ፀጥታ ሃይሎች ጭምር መቆጣጠር አልቻሉም፡፡ ደጋፊዎችም ወደ ሌሎች ቦታዎች እየሸሹ ይገኛሉ፡፡
እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
45+1′ አዳነ ግርማ ከፍፁም ቅጣት ምት የግራ ጠርዝ የመታው ኳስ ተደርቦ ወጥቶበታል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ጎልልል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
39′ መሃሪ ያሻማውን ኳስ አዳነ ሞክሮ ሲመለስበት ራምኬለል አግኝቶ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል፡፡
38′ ከበሃይሉ የተሻገረለትን ኳስ አዳነ በአክሮባቲክ ምት ሞክሮ ተከላካዮች ተደርበው አውጥተውበታል፡፡
ጎልልል!!!! አዳማ ከተማ
37′ ጫላ ድሪባ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ አዳማን ቀዳሚ አድርጓል፡፡
32′ ጨዋታው በአመዛኙ በአዳማ ግማሽ ሜዳ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
30′ ወንድወሰን ሚልኪያስ ወጥቶ ወንድሜነህ ዘሪሁን ገብቷል፡፡
28′ ራምኬል ግብ ለማስቆጠር የተመቻቸ ቦታ ላይ ሆኖ የመታውን ኳስ ሞገስ በጥሩ ሸርታቴ አድኖታል፡፡
23′ በሃይሉ ከቅጣት ምት ያሻማውን ኳስ አዳነ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
12′ በሃይሉ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ጃኮብ አውጥቶበታል፡፡
ተጀመረ
ጨዋታው ተጀምሯል፡፡ ጊዮርጊስ ከግራ ወደ ቀኝ ፣ አዳማ ከቀኝ ወደ ግራ ያጠቃሉ፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
ሮበርት ኦዶንካራ
አለማየሁ ሙለታ – ደጉ ደበበ – አስቻለው ታመነ – መሃሪ መና
ምንያህል ተሾመ – ተስፋዬ አለባቸው – ምንተስኖት አዳነ
ራምኬል ሎክ – አዳነ ግርማ – በኃይሉ አሰፋ
የአዳማ ከተማ አሰላለፍ
ጃኮብ ፔንዛ
እሸቱ መና – ምንተስኖት አበራ – ሞገስ ታደሰ – ሱሌማን መሃመድ
ታከለ አለማየሁ – ብሩክ ቃለቦሬ – ወንድወሰን ሚልኪያስ – ፋሲካ አስፋው – ጫላ ድሪባ
ታፈሰ ተስፋዬ