በቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ ደጋፊዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው እና የንብረት ጉዳቶች ደርሰዋል

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ስታድየም በቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ ከተማ ጨዋታ የመጀመርያ አጋማሽ በካታንጋ እና ሚስማር ተራ በኩል የተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች እና የንብረት ጉዳት አስከትሏል፡፡

ከመጀመርያው አጋማሽ የመጨረሻ ደቂቃዎች የጀመረው ግጭት ቀስ በቀስ እየተጋጋለ መጥቶ ለግማሽ ሰአት ያህል ድንጋዮች እና ወንበሮች አስከመወራወር የደረሰ ሲሆን በስፍራው የነበረው የፀጥታ ሀይል እጥረትም ግጭቱን አባብሶታል፡፡

በግጭቱ ጉዳት ደርሶባቸው በቤተዛታ ሆስፒታል ህክምና የተደረገላቸው ደጋፊዎች 21 ሲሆኑ አንድ ፌዴራል ፖሊስ በሁለቱም አይኑ ላይ መጋረድን ያስከተለ እብጠት ሲደርስበት ሌላው ፖሊስ ደግሞ ሁለት ጥርሶቹ ወልቀዋል፡፡

PicsArt_1460924190134

ጉዳት ከደረሰባቸው ደጋፊዎች መካከል ስንታየሁ ይሁነኝ ፣ አቤል አክሊሉ እና አዲስ ታዱ የተባሉ ተጎጂዎች የግሉኮስና የኦክስጅን እጥረት የነበረባቸው በመሆኑ እርዳታ ተደርጎላቸው ሆስፒታሉን ለቀዋል፡፡  አንድ ደጋፊ ደግሞ ራሱን ስቶ የነበረ በመሆኑ የህክምና ክትትል ተደርጎለት ወደ ቤቱ ተመልሷል፡፡

በአጠቃላይ የመፈንከት ፣ አጥሩን ለመዝለል ሲታገሉ በሽቦው እጅ የመቆረጥ እና የራስ ምታት ህመም ከደረሱት ጉዳቶች ዋንኞቹ ሲሆኑ በካታንጋ በርካታ ወንበሮች የመነቃቀልና የመሰበር እጣ ገጥሟቸዋል፡፡

PicsArt_1460924322863

PicsArt_1460924406263

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *