የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ነገ ወደ ጅቡቲ ያመራል

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከሶማልያ ጋር ለሚያደርገው የ2017 የአፍሪካ ከ20 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ነገ ወደ ጅቡቲ ያመራል፡፡

ያለፉትን 9 ቀናት በአዳማ ከትሞ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ብሄራዊ ቡድኑ ከሁለት ክለቦች ጋርም የወዳጅነት ጨዋታ አድርጓል፡፡ በዛሬው እለትም የመጨረሻ ልምምዱን በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም አድርጓል፡፡ 23 ተጫዋቾች በዛሬው ልምምድ ላይ ሲገኙ ቀላል ልምምዶች እና ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ግብ አክርሮ መምታትም በዛሬው ልምምድ ላይ ትኩረት የተደረገበት ነበር፡፡

PicsArt_1460997665951

ኢብራሂም ሁሴን ፣ ሱራፌል ዳንኤል እና ተመስገን ገብረኪዳን የፓስፖርት ጉዳዮችን ለማጠናቀቅ በልምምድ ላይ ያልተገኙ ሲሆን በመጀመርያው ጨዋታ ተሰልፎ የነበረው ተስፋዬ ሽብሩ በጉዳት ምክንያት ወደ ጅቡቲ የመሄዱ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ነገ ከቀኑ 8፡00 ላይ 20 ተጫዋቾችን ጨምሮ 25 የልኡካን ቡድን በመያዝ ወደ ጅቡቲ የሚያቀኑ ሲሆን አመሻሹ ላይ ቀላል ልምምድ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሃንስ ጨዋታውን አሸንፈው ለመመለስ ጠንካራ ዝግጅት ማድረጋቸውንና የቡድኑ መንፈስም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

PicsArt_1460997703043

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *