ቻምፒየንስ ሊግ፡ ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት የሚደረገው የመጨረሻ ትንቅንቅ ዛሬ ይጀምራል

የኦሬንጅ ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀምራሉ፡፡ በቻምፒየንስ ሊጉም ሆነ ኮንፌድሬሽን ካፑ ታሪክም ለመጀመሪያ ግዜ በሳምንት አጋማሽ ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ይሆናሉ፡፡

ለቻምፒየንስ ሊጉ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በሳምንቱ አጋማሽ የሚደረገው ጨዋታ በዛምቢያው ዜስኮ ዩናይትድ እና በማሊው ስታደ ማሊያን መካከል ይሆናል፡፡ ባማኮ ላይ 3-1 ያሸነፈው ዜስኮ በሜዳው እና ደጋፊው ፊት አሸንፎ ከ2009 በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ምድብ ድልድሉ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
image
image

ዛማሌክ ወደ ቤጃያ ያቀና ሲሆን መውሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያን ይገጥማል፡፡ በ2014/15 የውድድር አመት ድንቅ የነበረውን አጥቂውን ባሰም ሞርሲን የቀጣው ዛማሌክ የማለፍ ከፍተኛ ግምትን አግኝቷል፡፡ ዛማሌክ በመጀመሪያው ግጥሚያ 2-0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ ቤጃያ በአልጄሪያ ቻምፒዮናንት ናሽናል (ሞቢሊስ ሊግ) ስኬታማ ጉዞ ላይ መገኘቱ (በደረጃ ሰንጠረዡ ከመሪው ዩኤስኤም አልጀር በ12 ነጥቦች ርቆ 2ኛ ነው) ጨዋታውን ተጠባቂ እንዲሆን አድርጓታል፡፡ ካይሮ ላይ በነበረው ጨዋታ ድንቅ እንቅስቃሴ ያሳየው አማካዩ አይመን ሀፍኒ ጉዳት ላይ መገኘቱ አሰልጣኝ አሌክስ ማክሊሽን አሳስቧል፡፡ ሀፍኒ ከዛማሌክ ጋር ወደ አልጀሪያ የተጓዘ ሲሆን የመሰለፉ ነገር ግን አጠራጣሪ ነው፡፡
image
image

የምስራቅ አፍሪካ ተወካዩ ኤል-ሜሪክ ሴቲፍ ላይ ከአልጄሪያው ኢኤስ ሲቲፍ ጋር ይፋለማል፡፡ ኦምዱሩማን ላይ በነበረው ጨዋታ 2-2 የተለያዩት ኤል-ሜሪኮች በዛሬው ጨዋታ ላይ ግብ ለማስቆጠር አጥቅተው እንደሚጫወቱ ተናግረዋል፡፡ በአልጄሪያ ሊግ የሚዋዥቅ አቋም እያሳየ የሚገኘው ሴቲፍ ወደ ምድብ ማጣሪያው የመግባት ሰፊ ቅድመ ግምት አግኝቷል፡፡
image
image

የዛሬ ጨዋታዎች

15፡00 – ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) ከ ስታደ ማሊያን (ማሊ) [3-1] ሌቪ ማዋናዋሳ ስታዲየም

18፡00 – መውሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (አልጄሪያ) ከ ዛማሌክ (ግብፅ) [0-2] ስታደ ዩናይት መግሪቢን

19፡00 – ኢኤስ ሴቲፍ (አልጄሪያ) ከ ኤል-ሜሪክ (ሱዳን) [2-2] ስታደ 08 ሜይ 1945

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *