ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ 

የ2016 ኦሬንጅ ኮንፌሬሽን ካፕ የሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ በሚደረጉ ሶስት ጨዋታዎች ይጀምራሉ፡፡

የምስራቅ አፍሪካው ተወካይ አዛም ወደ ሶስተኛው የማጣሪያ ዙር ለማለፍ ከቱኒዚያው ኤስፔራንስ ጋር ይፋለማል፡፡ አዛም ዳሬ ሰላም ላይ ከኃላ በመነሳት 2-1 ያሸነፈ ሲሆን ቤድቬስት ዊትስ ላይ ሃትሪክ የሰራው ኮትዲቯራዊው ኪፕሬ ቲቼቲቼ በጉዳት ከቡድኑ ውጪ ሆኗል፡፡ በሴካፋ ውድድር የታንዛኒያን የፊት መስመር የመራው ጆን ቦኮ ከጉዳት ማገገም መጀመሩ እየሳሳ ለመጣው የአዛም የፊት መስመር መልካም ዜና ሆኗል፡፡ ኤስፔራንስ በቱኒዚያ የሊግ በተደረገ ጨዋታ በሰፊ ግብ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን የአጥቂ አማካዩ ፋክረዲን ቤንየሱፍ በጥሩ አቋም ላይ መገኘቱ ለቱኒዙ ክለብ የማለፍ ተስፋው እንዲሰፋ ያደረገዋል፡፡
image
image

ሌላኛው የቱኒዚያ ክለብ ስታደ ጋብሲየን የዛምቢያውን ዛናኮን ያስተናግዳል፡፡ በኮንፌድሬሽን ካፑ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በሳምንት አጋማሽ በሚደረገው ጨዋታ ጋብሲየን ሉሳካ ላይ ያሳካው የ1-1 ውጤት በመልሱ ጨዋታ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ እንዲጠበቅ አድርጓታል፡፡ ዛናኮ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ማሸነፍ ወይም 2-2 እና ከዚያ በላይ የአቻ ውጤትን ማስመዝገብ አለበት፡፡
image

image

ከአንጎላዋ የማዕድን ማውጪያ ከተማ የተገኘው ሳግራዳ ኤስፔራንሳ የማለፍ እድሉ የጠበበው የኮንጎ ብራዛቪሉ ቪታ ክለብ ሞካንዳን ያስተናግዳል፡፡ ኤስፔራንሳ ከሜዳው ውጪ 2-1 አሸንፎ የተመለሰ ሲሆን ከወዲሁ ወደ ሶስተኛው የማጣሪያ ዙር ለማለፍ የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
image

image

የዛሬ ጨዋታዎች

14፡30 – ስታደ ጋብሲየን (ቱኒዚያ) ከ ዛናኮ (ዛምቢያ) [1-1] ስታደ ኦሎምፒክ ደ ጋበስ

15፡30 – ሳግራዳ ኤስፔራንሳ (አንጎላ) ከ ቪታ ክለብ ሞካንዳ (ኮንጎ ብራዛቪል) [2-1] ኢስታዲዮ ሳግራዳ ኤስፔራንሳ

19፡00 – ኤስፔራንስ ሶፖርቲቭ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) ከ አዛም (ታንዛኒያ) [1-2] ስታደ ኦሎምፒክ ኖቬምበር 7 ራደስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *