ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-2 ደደቢት
4′ ሰናይት ቦጋለ
52′ ሎዛ አበራ
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በደደቢት 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ በሁለቱ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነትም ወደ 8 ሰፍቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
90+6′ ሰናይት ቦጋለ ወጥታ ትበይን መስፍን ገብታለች፡፡
90+2′ ትዕግስት ያደታ ከግቡ በቅርብ ርቀት ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ አግኝታ በግንባሯ የመታችው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
90+1′ ብርቱካን ገብረክርስቶስ ወጥታ ኪፊያ አብዱልከሪም ገብታለች፡፡ የብርቱካን ጉዳት በቀጥታ ወደ ሆስፒታል እንድትወሰድ አድርጓል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 6 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
87′ ዙለይካ ጁሃድ ወጥታ ቤዛዊት ተስፋዬ ገብታለች፡፡
ቢጫ ካርድ
86′ አዳነች ጌታቸው በብርቱካን ላይ በሰራችው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
83′ አልፊያ ጃርሶ ወጥታ የሺሃረግ ለገሰ ገብታለች፡፡
ቢጫ ካርድ
82′ መስከረም ኮንካ ኳስ አላግባብ በማዘግየቷ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡
76′ ጥሩአንቺ ከርቀት የሞከረችውን ኳስ ሊያ ሽብሩ ስትጨርፈው የግቡ አግዳሚ መልሶታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
74′ ብዙነሽ ሲሳይ ወጥታ አዳነች ጌታቸው ገብታለች፡፡
70′ ጨዋታው መሃል ሜዳ ቅቅብሎች ላይ ያመዘነ ሆኗል፡፡ ከ2ኛው ግብ መቆጠር በኋላ ይህ ነው የሚባል ሙከራ አልተደረገም፡፡
59′ ጨዋታው ከ6 ደቂቃ መቋረጥ በኀላ ተጀምሯል፡፡
-የንግድ ባንኮች ለግቡ መቆጠር ምክንያት የሆነው ቅጣት ምት ካለአግባብ ተሰጥቶብናል በሚል የክስ ሪዘርቭ አስይዘዋል፡፡
ጎልልል!!! ደደቢት
52′ ሎዛ አበራ ከቅጣት ምት የደደቢትን 2ኛ ግብ ከመረብ አሳርፋለች፡፡
ቢጫ ካርድ
50′ ብሩክታዊት ግርማ የዳኛን ውሳኔ ባለመቀበል የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመዞባታል፡፡
ተጀመረ!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀመረ
——
እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በደደቢት 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
-ጨዋታውን ለመመልከት ከወትሮው ቁጥሩ ከፍ ያለ ተመልካች በስታድየም ተገኝቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
35′ ወይንሸት ፀጋዬ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡
23′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ተጠቅማ ሽታዬ ሲሳይ ብትሞክርም ሊያ ይዛባታለች፡፡ በጨዋታው የሊያ ሽብሩ ትኩረት እና አቋቋም ግሩም ነው፡፡
-ንግድ ባንክ በፍጥነት የደደቢት የግብ ክልል በመድረስ ጥቃቶች በመሰንዘር ላይ ይገኛል፡፡
20′ ሽታዬ ሲሳይ ከግቡ በቅርብ ርቀት የሞከረችውን ኳስ ሊያ ይዛባታለች፡፡
18′ ሽታዬ በጥሩ ሁኔታ ያሻገረችውን ኳስ ረሂማ በአግባቡ ተቆጣጥራ ወደ ግብ አክርራ ብትመታም ሊያ ሽብሩ ይዛባታለች፡፡
ቢጫ ካርድ
6′ ኤደን ሽፈራው የመጀመርያውን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡
ጎልልል!!! ደደቢት
4′ ሰናይት ቦጋለ ተጫዋቾችን በማለፍ ከ16:50 ጠርዝ የመታችው ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አርፏል፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው በንግድ ባንክ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
**** በጋምቤላ ክልል በተፈፀመው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡
09:00 በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ልደታን 2-0 አሸንፏል፡፡
———
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ
22 ንግስት መዓዛ
10 ብዙነሽ ሲሳይ – 12 ጥሩአንቺ መንገሻ – 20 ፅዮን እስጢፋኖስ – 4 እታፈራሁ አድርሴ
14 ህይወት ደንጊሶ – 7 ዙለይካ ጁሃድ – 8 ትግስት ያደታ
11 ሽታዬ ሲሳይ – 9 ረሂማ ዘርጋ (አምበል) – 16 ብሩክታዊት ግርማ
የደደቢት አሰላለፍ
24 ሊያ ሽብሩ
17 ዘቢብ ሃ/ስላሴ – 3 ወይንሸት ፀጋዬ – 4 መስከረም ኮንካ – 13 አስራት አበበ
16 አልፊያ ጃርሶ – 2 ኤደን ሽፈራው (አምበል) – 15 ሰናይት ቦጋለ
14 ሰናይት ባሩዳ – 12 ሎዛ አበራ – 11 ብርቱካን ገ/ክርስቶስ